Coming Up Fri 10:00 PM  AEDT
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio
ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ሕልሜ ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲያብብ ነው።” - አበበ ጽጌ

አበበ ጽጌ

የሕይወት ጉዞ ከውልደት እስከ ዕድገት የራሷን ምዕራፍ እየከፈተችና እየዘጋች ትረማመዳለች። የትናንት ሕይወት - የዛሬ ትውስታ ይሆናል። ስለ መጪው የሚያውቅ የለም። ምኞትና ተስፋን ከማሳደር በስተቀር። የዛሬው “አገር ቤትና ባሕር ማዶ” ወር ተረኛ አቶ አበበ ጽጌ ናቸው። የሕይወት ጉዞ ትረካ መነሻቸው የትውልድ ቀዬአቸው ወልቂጤ ነው። በስደት ሕይወት ምልሰታዊ ምልከታቸው ወደ ሱዳን አሻግረው፣ በኒውዚላንድ አቋርጠው፤ የአገረ አውስትራሊያ ሕይወታቸውን ከኢሕአፓ ትግላቸው ጋር አጣቅሰው ያወጉናል።

አቶ አበበ በለጋ ሕይወታቸው የ1966ቱን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮት ንቅናቄ ተከትሎ በወቅቱ ስመ ገነን የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ወጣቶች ክንፍ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ወጣቶች ሊግ (ኢሕአወሊ) አባል ሆኑ።

My Story Abebe Tsige
የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Courtesy of PD

 እንደ ዘመናቸው ወጣቶች ኢትዮጵያን በሶሻሊስታዊ ሥርዓት ለመታደግ።

 ሆኖም፤ የመጨረሻው የኢትዮጵያ ዘውዳዊ የአገዛዝ ሥርዓት ሲያከትም ሥልጣነ መንግሥቱ በወቅቱ አዲስ በተመሠረቱት የፖለቲካ ድርጅቶች እጅ ሳይሆን በአገሪቱ የጦር ኃይሎች መዳፍ ስር ወደቀ።

 የወጣቱ አበበ ጽጌ ፓርቲ - ኢሕአፓም ዋነኛ የፖለቲካ ስልጣን ተቀናቃኝ ሆኖ ቀረበ። “ያለ ምንም ደም - ኢትዮጵያ ትቅደም” የተዘመረለት አብዮት አያሌ ወጣቶችን ለእሥራት፣ ስደትና ሕልፈተ ሕይወት ዳረገ።

 የወጣቱ አበበ ዕጣ ፈንታም እሥራትና ስደት ሆነ።

 የሱዳን አጎራባቿ ጎንደር፤ ለአቶ አበበ የኢትዮጵያን ድንበር በእግር መሻገሪያ ሆነች። የሱዳን ምድርም ወጣቱ አበበን ከባላገርነት ወደ ስደተኛነት ለወጠች።

 ለስደት ያበቃቸው ፖለቲካዊ አተያይና የኢሕአፓ አባልነታቸው ሱዳንም አልለያቸው አለ።

 ይሁን’ጂ ከሱዳን አውጥቶ ለኒውዚላንድ፣ ሲልም፤ ለአገረ አውስትራሊያ ነዋሪነትና ቤተሰብ ምሥረታ አብቅቷቸዋል።

My Story Abebe Tsige
አበበ ጽጌና ቤተሰቦቹ
Courtesy of AT

 አገሩን ለሚያፈቅር ሰው ባሕር ማዶኛነት አገሩን ከውስጡ አስወጥቶ አያስረሳምና፤ አቶ አበበ ዛሬም - ከአድማስ ባሻገር ስለ አገራቸው መልካሙን ያልማሉ።

 ኢትዮጵያዊነት በምድረ ኢትዮጵያ እንዲያብብ።

የለጋ ወጣት ሕይወት ምኞታቸውም በአገረ ኢትዮጵያ ዕውን ሆኖ ለማየት ተስፋ ያደርጋሉ።

 ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ቆሞ፤ ፍትሓዊ እኩልነት ሰፍኖ።

 እስከዚያው ድረስ ግና ባሉበት አገረ አውስትራሊያ ለኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ የበኩላቸውን አስተዋጽዖዎች በመቸሩ ይገፋሉ።

Coming up next

# TITLE RELEASED TIME MORE
አገር ቤትና ባሕር ማዶ - “ሕልሜ ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲያብብ ነው።” - አበበ ጽጌ 06/09/2019 14:32 ...
የእሳት አደጋ ባለሥልጣናት ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ለቅቀው ለመውጣት ስንዱ እንዲሆኑ እያስጠነቀቁ ነው 11/11/2019 05:18 ...
“ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የተማሩ ብቻ ሳይሆን የተመራመሩና ተሞክሮ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያስፈልጓቸዋል።” - ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ 11/11/2019 34:11 ...
"የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስቀጠል አብረን እንሥራ።” - ዶ/ር ሺፈራው ገሠሠ 10/11/2019 17:54 ...
** ባለ ሥልጣናት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ማኅበረሰባትን ብርቱ የእሳት ቃጠሎ እንደሚገጥማቸው እያስጠነቀቁ ነው ... ** የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ፓርቲያቸውን ለመልካም ዕድል የሚያበቃ ግዙፍ ፖሊሲ ይፋ ሊያደርጉ ነው ... 08/11/2019 05:15 ...
“ኢትዮጵያን እንገንባ እንጂ አናፍርሳት፤ ይህችን አገር ማዳን አለብን።” - የአገር ሽማግሌዎች 08/11/2019 38:56 ...
የአረጋውያን መጦሪያዎች ባሕልና ቋንቋን እንዲያካትቱ እየተመከረ ነው 08/11/2019 04:55 ...
“በኢትዮጵያ ሕዝብና መከላከያ ላይ እምነት አለኝ።” - ተድላ አስፋው 07/11/2019 25:51 ...
** ጠ/ሚ/ር ስኮት ሞሪሰን የአመለካከት ልዩነቶች የአውስትራሊያና ቻይናን ግንኙነት እንዳያውክ እንደሚተጉ አስታወቁ ... ** የግብረ አካል ጉዳተኞች ሮያል ኮሚሽን የመጀመሪያ ቀን ስሚውን ጀመረ ... 04/11/2019 06:19 ...
“ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነው።” - በሪሁን ደጉ 04/11/2019 12:14 ...
View More