ቅዳሜ ሜይ 21 / ግንቦት 13 በተካሔደው የአውስትራሊያ አገር አቀፍ ምርጫ የሌበር ፓርቲ ለአሸናፊነት በቅቷል። በምርጫ ዘመቻው ወቅት ቃል ከገባቸው ፖሊሲዎቹ አንዱ የኡሉሩ መግለጫን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅ ማስገኘት ነው። አንቶኒ አልባኒዚ ዛሬ ከቀትር በፊት 31ኛው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላም ዳግም ያረጋገጡት ይህንኑ የኡሉሩ መግለጫ ሙሉ በሙሉ ግብር ላይ ማዋል ነው።
ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
የኡሉሩ መግለጫ
A sunset view of Uluru as seen from the designated viewing area on August 12, 2019 in the Uluru-Kata Tjuta National Park, Australia. Source: Getty