በወርኃ ታህሳስ የመጀመሪያ ሳምንት ላይ በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሞጣ ከተማ እምነት ቤቶችና የንግድ ሱቆች በእሳት ጋይተዋል። በአፀፋውም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሞጣ ነዋሪዎችና የባሕር ማዶ ኢትዮጵያውያንን አካትቶ ፈጣን ውግዘትና የማረጋጊያ ምክረ ሃሳቦችን አሰንዝሯል። ስለ ደረሱት ጉዳቶች፣ ሕዝብ - ለሕዝብ እየተካሄዱ ስላሉት ግንኙነቶችና የመልሶ ማቋቋም ጥረቶችን አስመልክተን፤ ከአቶ ኃይሉ ያዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ ከአቶ ዑመር መኮንን - በአዲስ አበባ የሞጣ ሙስሊም ተወላጆች ኮሚቴ አስተባባሪና ከአቶ አበባው ቢምር - የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር ተነጋግረናል።
“ሞጣ ያለው ሙስሊም ማኅበረሰብ አቅም ስለሌለው መስጊዶችን የክልሉ መንግሥት ያሠራልን” - አቶ ዑመር መኮንን
Source: Courtesy of PD and AA