Coming Up Fri 10:00 PM  AEDT
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio
ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

“ባልሰለጠነ ዘመን የሰለጠነ ሃሳብ ሰጥተውን ያለፉ አባቶቻችን ዕዳ አለብን።” - ሰብለወርቅ ታደሰ

Seblewerk Tadesse

የዛሬ “አገር ቤትና ባሕር ማዶ” እንግዳችን ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ናቸው።የግለ-ታሪክ ትረካቸው መነሻ የትውልድ ሠፈራቸው የሆነችው ቤልኤይር ናት። የኢትዮጵያ መዲና ከሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ ነው የምትገኘው።

ትምህርት ባለ ሁለት ወገን ስለት ያለው ነውና በግለሰብ አዕምሮ ውስጥ ሰርፆ ዓለምን በአዎንታዊና አሉታዊ ገፁ ይቀርፃል፤ ይለውጣል።

ትንሿ ሰብለ እግሮቿ ወደ ቀበና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካመሩበትና ጉብሏ ሰብለ በኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአዕምሮ ጉልምስና ከደረሰችበት ጊዜ አንስቶ ውስጣዊ ቅርጽና ይዘታቸው የታነፀው በአዎንታዊነት ነው።

በዘመነ ጉልምስናም የሰብለወርቅ ዕሳቤ በአድማስ ዩኒቨርሲቲ የግብይት አስተዳደር ዲግሪ ምልከታ ብቻ አልተወሰነም። ገፍቶ-ዘልቆ የአካዳሚ ነፃነት ዋጋን ለመረዳት፣ በሃሣብ የበላይነት ለማመን፣ ላለመስማማት የመስማማትን አቅምን በማዳበር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ እንጂ በአመፅ መከሰት የለበትም የሚሉ አተያዮቻቸውን አዳብሯል።

ያም የዲሞክራሲ መሠረት ለሆነው ለማኅበራዊ ፍትሕ ጥያቄ አንጋቢነት አነሳስቷቸዋል። ከቃለ - ነቢብ ወደ ግብርም አሸጋግሯቸዋል። በ2004 የቀስተ ደመና ፓርቲን በወጣቶች ሊግ አደራሽነትና ሲልም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የድርሻቸውን ተወጥተዋል።

ቀስተደመና የቅንጅት ፓርቲ አካል ሲሆንም፤ በ’97ቱ ምርጫ በአዲስ አበባ አራዳና አዲስ ከተማ አደራጅተዋል።

My Story: Seblewerk Tadesse
Courtesy of PD

ይሁንና የ’97ቱ ምርጫ ቅንጅትን ለሩቅ አሳቢ - ቅርብ አዳሪነት በመዳረጉ፤ እሳቸውን ጨምሮ የአመራር አካላቱ ዘብጥያ ወርደዋል። ከ18 ወራት ፈታኝ የእሥር ሕይወት በኋላ ግና ለስደት ሕይወት ግድ ተሰኝተዋል።

የፍቅሯ ግለት እስከ ዛሬም ውስጣቸው ግሎ ያለችውን የውድ አገራቸውን ኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው ወደ ኬንያ ገቡ። ጥቂት ቆይቶም ኡጋንዳ ዘለቁ። ኡጋንዳ ሳሉ ቀናትና ሳምንታት በወራት እየተቆጠሩ ሳለ፤ ስደተኛነታቸው በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን በኩል ዕውቅና ተቸሮት ነበርና የአውስትራሊያ ዳግም ሠፈራ ቪዛ ተቸራቸው።

እርግጥ ነው፤ አገረ አውስትራሊያ ውስጥም ሆነው ለፍትሕ ድምፃቸውን ከማሰማት ቸል አላሉም።

My Story: Seblewerk Tadesse
Seblewerk Tadesse
Courtesy of ST

አፍታም ሳይቆዩ ወደ ማኅበራዊ ሥራ ግልጋሎት ተሰማርተው ለቤት ውስጥ አመፅ ሰለባነት የተዳረጉ ኢትዮጵያውያንና አውስትራሊያውያን ሁኔታ ግና ሕሊናቸውን ሞግቷል።

ሆኖም ችግር አግናኝ ሳይሆኑ፤ ከቶውንም የመፍትሔ አካል ለመሆን በደቡብ ማኅበረሰብ የፕሮጄክት ሥራ አስኪያጅነታቸው ለቤት ውስጥ አመፅ ጥቃት ተጎጂዎች እገዛ በማድረጉ ዘርፍ አስተዋፅዖዎችን እያበረከቱ ይገኛሉ። ያም አንዱ ከማኅበረሰባዊ ግልጋሎቶች የሚመነጭ የመንፈስ እርካታ ማግኛና ዕሴቶቻቸውን መተግበሪያ ሆኗቸዋል።

የኩዊንስላንድ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማኅበር አመራር አካል በመሆንም ንቁ ተሣትፎ አበርክተዋል።

በግል ሕይወታቸው አውስትራሊያ ከማለፊያ የሕይወት ጓደኛ ጋር አጣምራ በሁለት ልጆች እናትነታቸውን የአብራካቸውን ፍሬ እንዲያዩ አብቅታቸዋለች።

My Story: Seblewerk Tadesse
Seblewerk Tadesse with her children
Courtesy of ST

Coming up next

# TITLE RELEASED TIME MORE
“ባልሰለጠነ ዘመን የሰለጠነ ሃሳብ ሰጥተውን ያለፉ አባቶቻችን ዕዳ አለብን።” - ሰብለወርቅ ታደሰ 04/11/2019 27:53 ...
የኢትዮጵያ ለውጥ ሂደትና የአንቂዎች ሚና 21/11/2019 44:30 ...
የእሳት አደጋ ባለሥልጣናት ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ለቅቀው ለመውጣት ስንዱ እንዲሆኑ እያስጠነቀቁ ነው 11/11/2019 05:18 ...
“ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የተማሩ ብቻ ሳይሆን የተመራመሩና ተሞክሮ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያስፈልጓቸዋል።” - ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ 11/11/2019 34:11 ...
"የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስቀጠል አብረን እንሥራ።” - ዶ/ር ሺፈራው ገሠሠ 10/11/2019 17:54 ...
** ባለ ሥልጣናት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ማኅበረሰባትን ብርቱ የእሳት ቃጠሎ እንደሚገጥማቸው እያስጠነቀቁ ነው ... ** የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚ ፓርቲያቸውን ለመልካም ዕድል የሚያበቃ ግዙፍ ፖሊሲ ይፋ ሊያደርጉ ነው ... 08/11/2019 05:15 ...
“ኢትዮጵያን እንገንባ እንጂ አናፍርሳት፤ ይህችን አገር ማዳን አለብን።” - የአገር ሽማግሌዎች 08/11/2019 38:56 ...
የአረጋውያን መጦሪያዎች ባሕልና ቋንቋን እንዲያካትቱ እየተመከረ ነው 08/11/2019 04:55 ...
“በኢትዮጵያ ሕዝብና መከላከያ ላይ እምነት አለኝ።” - ተድላ አስፋው 07/11/2019 25:51 ...
** ጠ/ሚ/ር ስኮት ሞሪሰን የአመለካከት ልዩነቶች የአውስትራሊያና ቻይናን ግንኙነት እንዳያውክ እንደሚተጉ አስታወቁ ... ** የግብረ አካል ጉዳተኞች ሮያል ኮሚሽን የመጀመሪያ ቀን ስሚውን ጀመረ ... 04/11/2019 06:19 ...
View More