የጤና ለጣና አውስትራሊያ - የዕምቦጭ አረም በጣና ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቅረፊያ ያግዝ ዘንድ ኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያንን አስተባብሮ $33,536.56 ካሰባሰበ አንድ ዓመት ሊሞላው የአንድ ወር ፈሪ ላይ ይገኛል። ገንዘቡ አሁንም ድረስ ከአውስትራሊያ ባንክ ወጥቶ ለታለመለት ተግባር አልዋለም። የጤና ለጣና አውስትራሊያ ሊቀመንበር - ዶ/ር አደራጀው ታክሎ፣ ጸሐፊ ዶ/ር ሱራፌል መላኩና ዐቃቤ ንዋይ ዶ/ር ሰሎሞን ዋስይሁን፤ ባለፉት 11 ወራት ጤና ለጣና አውስትራሊያ ስለከናወናቸው እንቅስቅሴዎቹ፣ ጥረቶቹና የወደፊት ትልሞቹ ያናገራሉ። የተሰባሰበው ገንዘብም ግብር ላይ እንዲውል ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።
“እባካችሁን የአማራ ክልልና የፌዴራል መንግሥታት - የጣናን የዕምቦጭ ችግር ለመቅረፍ ያሰባሰብነውን ከ33 ሺህ በላይ ዶላር ከእጃችን አውጡልን።” - ጤና ለጣና አውስትራሊያ
Dr Aderajew Taklo (L), Dr Solomon Wassyihun (C), and Dr Surafel Melaku (R) Source: Courtesy of AT and SBS Amharic