ዕንቁጣጣሽን በወርኃ መስከረም ለምታከብሩ ሁሉ የሞቀ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።
ይህ ልዩ ወቅት የኢትዮጵያ ዘመን መቁጠሪያ የሚንጸባረቅበት፤ ቤተሰቦች ተሰባስበው በጋራ ቅርስና ባሕላቸውን የሚያከብሩበት ልዩ በዓል ነው።
እንዲሁም፤ በሕብረት አሰናስሎ ያያያዘን የጋርዮሽ ዕሴታችን የሆነው የአውስትራሊያን የበለጸገ መድብለ-ባሕላዊ ድርና ማግን ልብ ማሰኛ ነው።
የአውስትራሊያ ቃል ኪዳን የሆነው - ሁላችንም በሐሴት የምንመላበት ልዩ ጥቅምና ኃላፊነት - በእምነትና ባሕላዊ የመደብ ጀርባ ያልተገደበ አንዳችን አንዳችንን የምንቀበልበትና የምንከበርበት።
ለዚህም ነው፤ ከመላው ዓለም ሰዎች ወደ አውስትራሊያ ዘልቀው - አገሬ ብለው የሚጠሯትና በምድር ላይ በጣሙን ሰላማዊና ስሙም መድብለ-ባሕላዊ አገራት መካከል አንዱ ለመሆን የበቃነው።
የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ ለዝንቅ ሕብረተሰባችን ስኬት፤ እንዲሁም አገራችን ከኢትዮጵያ ለምትጋራው ወዳጅነት ላበርከቱት አስተዋጽዖ ዕውቅናን እቸራለሁ።
አዲሱን ዓመት ለማክበር በጋራ ስትሰባሰቡ፤ በተስፋና በአዲስ መንፈስ እንድትመሉ፤ ከቤተሰብና ማኅበረሰባችሁም ጋር በመልካም ወዳጅነት እንደምትታደሱ ተስፋ አደርጋለሁ።
ስኮት ሞርሰን
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር