የዛሬውን የውይይት መድረክ ፕሮግራማችንን ማርች 8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለመዝከር ይሆን ዘንድ ብለናል። የተሻለች አለምን ለማምጣት የምንፈለግ ከሆነ የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ የግድ ነው። ይህንን ተግባር ሴቶች ብቻ የሚወጡት ሳይሆን ወንዶችም በጋራ በቅንነት ሊሳተፉበት የሚገባ አላማ ነው። በአጠቃላይ በማህበረሰቡ ዘንድ ስር ሰድዶ የተንሰራፋውን ሴቶችን የማሳነስ ፤አይችሉም የማለት፤ ሳይመዘኑ መፈረጅ የመሳሰሉትን ጎታች አስተሳሰቦች ለማስወገድ ሁሉም በጋር መስራት እንዳለበት የውይይታችን ተሳታፊዎች ያምናሉ።የውይይታችን ተሳታፌዎች :- ወ/ሮ ብርቱካን ሽታዬ ቢያድግልኝ በቢሮ ኦፍ ሚቲሪዮሎጂ ክላይሜት ስፓሻል ዳታ የቡድን መሪ እንዲሁም በጂ ፒ ኤስ ሚቲሪዮሎጂ ተመራማሪወ/ሮ እመቤት ታደሰ በናሽናል አውስትራሊያ ባንክ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አማካሪ ናቸው። “ በመላው አለም ለሚገኙ ሴቶች እና ለሴቶች እኩልነት ተቆርቋሪ ወንዶች ሁሉ “መልካም የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 “ ይሁን ::
የውይይት መድረክ “ የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8” - ክፍል ሁለት
LR: Bertukan and Embet Source: SBS Amharic