"የሩስያና የዩክሬይን ጦርነት የፈጠረው የቀውስ አጋጣሚ ኢትዮጵያውያን የተፈጥሮ ሃብታችንን እንድንጠቀምና ምርታማነት ላይ እንድንሠራ የምናስብበት ጊዜ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ የሚችለው ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ተነጋግሮ ድጎማ የሚያግኝበትንና ምርት በርካሽ ከውጭ ገበያ የሚያገዛበትን አማራጮች ሲፈልግ ነው" ዶ/ር ዮናታን ድንቁ
ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ አምባው - በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ንግድ ተመራማሪና መምህር፤ የዩክሬይንና ሩስያን ጦርነት ተከትሎ የግጭቱ መቀስቀስና በሩስያ ላይ የተጣሉ ዘርፈ ብዙ ማዕቀቦች ለዋጋ ግሽበት አስባብ ሆነው በተለይ በአውስትራሊያ፣ ኢትዮጵያና አፍሪካ ላይ ስላሳደሯቸው የኑሮ ውድነቶች ያስረዳሉ።
አንኳሮች
- የዋጋ ግሽበት ምንነትና መንስኤዎች
- የኑሮ ውድነትና የዝቅተኛ ገቢ ተዳዳሪዎች
- የኑሮ ውድነት በአውስትራሊያ