"የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት ማሳደጉ እጅግ በጣም የሚበረታታ ተግባር ነው። በቀስታና በጥንቃቄ የብር ምንዛሪ እንዲቀንስ ማድረግ በጣም መጥፎ ነው ብዬ አላስብም" ዶ/ር ደሴ ታርቆ አምባው
ዶ/ር ዮናታን ድንቁ - በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ እና ዶ/ር ደሴ ታርቆ አምባው - በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ንግድ ተመራማሪና መምህር፤ የዩክሬይንና ሩስያን ጦርነት ተከትሎ የግጭቱ መቀስቀስና በሩስያ ላይ የተጣሉ ዘርፈ ብዙ ማዕቀቦች ለዋጋ ግሽበት አስባብ ሆነው በተለይ በአውስትራሊያ፣ ኢትዮጵያና አፍሪካ ላይ ስላሳደሯቸው የኑሮ ውድነቶች ያስረዳሉ።
አንኳሮች
- የውጭ ምርቶች ግብአትና የውጭ አቅርቦት
- የውጭ ምንዛሪና የብር ምዛሪ ተመን ቅነሳ
- የዋጋ ግሽበትና አፍሪካ