Coming Up Mon 10:00 PM  AEST
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio
ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

ሔርሞንና ኤደን፤ የአልኮል ሱስና የፍቅር ፈተና

Hermon Gashaw (L), and Eden Roma (L). Source: H.Gashaw and E.Roma

ሔርሞን ጋሻውና ኤደን ሮማ ከሱስ በመላቀቅና በፍቅር ፀንቶ በመቆየት ተፈትነዋል።ሔርሞን ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ፤ ኤደን በገደብ የለሽ ፍቅር የሕይወቷ ማዕከል ለመሆን የበቃውን ሔርሞንን ለመታደግ።

ፍቅር ለስኬት ሲበቃ በጣፋጭ ሕይወት ውስጥ ያኖራል። ክሽፈት ሲገጥመው ለልብ ስብራት ይዳርጋል።

በሁለቱም መንገዶች የሕይወት ስንክሳሮች ብዙ ናቸው።

ፍቅር ስሜትን ያውካል፣ የማንነት ዕሴቶችን ይፈትናል፣ ኅሊናን ይሞግታል፣ ለተስፋ መቁረጥ ይዳርጋል፤ ሲልም የሰላምና የጠብም ምንጭ እስከ መሆን ያደርሳል።  

የእውነተኛ ፍቅርን ጣዕም ለማጣጣምና ለመኖር ሕይወቱንም ለመኖር የሚበቁት ጥቂቶች የሚሆኑትም ለዚህ ነው። 

ሔርሞንና ኤደን ከጥቂቶቹ የሚደመሩ ናቸው።

"ጠጪ ከሚባሉት በላይ የምጠጣ ነበርኩ"

ሔርሞን መጠጥ የለመደውና ለሱሰኝነትም የበቃው ኢትዮጵያ ሳለ ነው። መነሻውም የቤት አረቄ ነው። 

እ.አ.አ በ2015 ወደ አውስትራሊያ ከመጣ በኋላ ግና "ሰው ኑሮውን ይመስላል" እንዲሉ ወደ ቢራና ውስኪ ተሸጋገረ።   

ጠጥቶ ማሽከርከር በብርቱ ጥብቅ የሆነባት አገረ አውስትራሊያ ሕግ ግና አላገደው።

እንደ አያሌ ዕለተ ሕይወቱ ሁሉ በአንዲቷ ቀን ከማለዳው መጠጣት ጀመረ። ከቀትር በኋላ ሠርግ ቤት አከለበት።

ምሽት ላይ ከአንድ የመዝናኛ ቤት የማሳረጊያ አልኮል ተጎንጭቶ እንደወጣ መኪናውን አጋጭቶ ለሆስፒታል በቃ። 

እግሮቹ በጣም ተጎድተው ስለነበርም በምርኩዝ ለመሔድ ግድ ተሰኘ።

Community
Hermon Gashaw.
H.Gashaw

"እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል"

ኤደን ሮማ የሔርሞን እህት ጓደኛና የቤተክርስቲያን ዘማሪ ናት።

የመኪና አደጋውን አስደንጋጭ ዜና ሰምታ ከእህቱ ጋር ሔርሞንን ጥየቃ ወደ ሆስፒታል ሔደች።

የደረሰበትን ጉዳት ስታይ ልቧ አዘነ። ከዚያ በፊት ተሰምቷት የማታውቀው ዓይነት ስሜትም ውስጧን አወከው።

ከሆስፒታል ተሰናብታ ቤቷ ከተመለሰች በኋላም ስለ ሔርሞን ማሰቧን ቀጠለች።

ዕሳቤዋ ውስጥ ገዝፎ ይታያት የነበረው የሕመምተኛ ፊቱ፣ በጄሶ ተጠቅልሎ የተሰቀለ ጉዳተኛ እግር፣ በሕመምና በድካም የዛለ አካል ሳይሆን፤ ከቶውንም ማግኔታዊ ስህበት ያለው ወጣት ገፅታ ነበር።   

ወደ ውስጧ ተመለከተች። ስሜቷን ጠየቀች። 

አዕምሮዋ ስሜቷ በርህራሄ መመላቱን አመላከታት።

ልቧ ፍቅር ላይ መውደቋን ትንፋሽን ቁርጥ - ቁርጥ በሚያደርግ ትርታው ነገራት።

ልቧን አመነች።

"ፍቅር ይዞኛል" ብላ ለራሷ አረጋገጠች።

እውነት ነበር። 

***

ሔርሞንም በበኩሉ በኤደን ውብ ገፅታ ልቡ መማለሉ ገባው። 

ከአንደበቷ ይፈልቁ የነበሩ 'አይዞህ ባይ' ቃላት ለጆሮ የሚጥም ጥዑም የሙዚቃ ቃና ሆነው ተሰሙት።

"በሕይወቴ እንዲህ ያለ ሁኔታ ገጥሞኝ አያውቅም። ይህች ልጅ ልታመልጠኝ አይገባም" ሲል ለራሱ ነገረ።

እንዳታመልጠውም ብዙ ርቀት ተጓዘ...

  

  

   

   

Coming up next

# TITLE RELEASED TIME MORE
ሔርሞንና ኤደን፤ የአልኮል ሱስና የፍቅር ፈተና 18/03/2022 15:31 ...
" በሜልበርን የተደረገው ሰልፍ አላማ በወለጋ በአማራ ብሄር ላይ የተደረገውን ዘር ተኮር ጥቃት ለመቃወም ነው። " - አቶ ግርማ አካሉ የአማራ ህብረት በሜልበርን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ 26/06/2022 13:03 ...
ዳባሳ ዋቅጅራ፤ ከስደት ወደ ሠፈራ 24/06/2022 15:16 ...
ዜና 24/06/2022 04:51 ...
ዳባሳ ዋቅጅራ፤ ከዘመቻ ወደ ስደት 24/06/2022 12:52 ...
ዳባሳ ዋቅጅራ፤ ከጥቁር እንጪኒ እስከ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 24/06/2022 11:32 ...
ቤንዴሬ ኦቦያ፤ ኢትዮጵያዊቷ የአውስትራሊያ ብሩህ ኮከብ አትሌት 22/06/2022 12:35 ...
የስደተኞች ቀን ታሪክ ምዝገባ፤ ፋቲማ ፔይማን የመጀመሪያዋ ሂጃብ ለባሽ የፓርላማ አባል ሆኑ 20/06/2022 07:09 ...
አዲስ አበባን ጨምሮ ተከሰተ የተባለው የዶሮ በሽታ ስጋት ማሳደሩ ተገለጠ 20/06/2022 09:10 ...
የሠፈራ መምሪያ፤ የስደተኞች ሳምንት 2022 በጋራ "የመፈወስ" አጋጣሚ 19/06/2022 08:16 ...
View More