መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሃዲስ ኪዳን መምህር፤ስለ የአውስትራሊያ ጉዟቸው ዓላማ፣ የሁለቱ ሲኖዶሶች አንድነትና የስደት ሕይወትን አስመልክተው ይናገራሉ። መጋቢ ሐዲስ የአውስትራሊያ ቆይታቸው ዘለግ ላለ ጊዜ ቢታቀድም በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የግልጋሎት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ግድ ተሰኝተዋል።
“በኢትዮጵያ የታየው ያለመቻቻልና የጽንፈኝነት መንፈስ ለዘመናት ተዳፈኖ የቆየ እንጂ አዲስ አይደለም” - መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
Megabi Hadis Eshetu Alemayehu Source: Martha Tsegaw