እህትማማቾቹ ኢትዮጵያውያን የጁ ጂትሱ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች መስከረምና ፀሐይ ዓለማየሁ ይባላሉ። መስከረም በአፍሪካ ሻምፒዮና የብርና ነሐስ ሜዳል ባለቤት ስትሆን፤ ወርሃ ጁላይ ላይ በአገረ አሜሪካ በሚከናወነው የዓለም ጁ ጂትሱ ሻምፒዮና ላይ አፍሪካን ወክላ ትፎካከራለች። እህት ፀሐይ ከአንድ ሳምንት በኋላ አንጎላ በሚካሔደው የጁ ጂትሱ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ለመገኘት በመሰናዶ ላይ ናት። አጋዥ ፌዴሬሽን ስለሌላቸው የወገን ድጋፍን ጠያቂ ናቸው።
አንኳሮች
- እህትማማቾችና የብራዚል ጁ ጂትሱ
- ውድድር፣ ስኬትና ዳግም መሰናዶ
- ወገን ለወገን