በአርቲስት ቴዲ አፍሮ "ፍቅር፣ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት" መርህ ላይ የተመሠረተው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን አድናቂዎች ማኅበር "አለሁ ለወገኔ" በሚል መሪ ቃል ከሰብዓዊ ድጋፍ ጥምረት ጋር በጋራ ለተፈናቃይና ተጎጂዎች መርጃ የሚውሉ አልባሳት፣ የግል ንፅህና መጠበቂያና ምግቦችን አሰባስቧል። እሑድ ታሕሳስ 3 የተካሔደውን "የአለሁ ለወገኔ" የበጎ አድራጎት ክንውንን አስመልክቶ የማኅበሩ መሪና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ምስክር ታደሰ ያስረዳሉ።
የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን አድናቂዎች ማኅበር የሩብ ሚሊየን ችሮታዎችን ለተፈናቃዮችና ተጎጂዎች አሰባሰበ
Source: M.Tadesse