የአለማቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ጽንሰ ሃሳብ ከሃያኛው ምእተ አመት መባቻ ጀምሮ ለሴቶች መብት በሚያቀነቅኑ ሴቶች ተጸንሶ ዛሬ በይፋ ለመከበር የበቃ በአል ቢሆንም ፤ የጾታ እኩልነት ግን ዛሬም ድረስ አልተረጋገጠም ። ዛሬም ድረስ ከ30 አገራት በላይ በሴቶች ላይ ግርዛትን እንደሚፈጽሙ ይታመናል ። በአለማችን በ2030 የሴት ልጅ ግርዛት ሙሉ ለሙሉ ይቆማል ተብሎ ግምት የተቀመጠ ሲሆን ለውጤታማነቱም ትምህርት አስፋላጊ መሆኑን ወ/ሮ ንግስቲ መልሆላንድ ይናገራሉ ።