ኩዊንስላንድን ክፉኛ ባጥለቀለቀው ጎርፍ ሳቢያ አያሌ ለጎርፍ ተጋላጭ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬዎቻቸው ተፈናቅነዋል። ወ/ሮ ያኔት ኪሮስና ቤተሰባቸው ከጎርፍ ሰለባዎቹ አንዱ ናቸው። ጎርፉ በእሳቸውና ቤተሰባቸው መኖሪያና ንብረት ላይ ስላደረሰው ጉዳትና ተጠልለው ስለሚገኙበት ሁኔታ ይናገራሉ። እርዳታ ላደረሱላቸው ወገኖችም ምስጋናም ያቀርባሉ።
አንኳሮች
- የጎርፍ አደጋ
- ሕይወትና ንብረት
- የማኅበረሰብ እርዳታ