ዮዲት እሸቱ፤ የፍቅርና ሰላም የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ግልጋሎት የምታቀርበው በምግብ አዳራሽ ሳይሆን በፌስቲቫልና ገበያ ሥፍራዎች በመዘዋወር ነው። ቅዳሜ ሜይ 7 ሲድኒ ኦሎምፒክ ፓርክ በሚካሔደው የአፍሪካ ባሕላዊ ፌስቲቫል ላይም ተገኝታ የኢትዮጵያን ባሕላዊ ምግቦች ለኢትዮጵያውያውያንና ለፌስቲቫሉ ታዳሚ አውስትራሊያውያን በሙሉ ለማቅረብ ስንዱ ስለመሆኗ ትናገራለች።
አንኳሮች
- የፍቅርና ሰላም ምግብ ቤት ምሥረታ
- የኢትዮጵያ ባሕላዊ ምግቦች አቅርቦት
- የሲድኒ የአፍሪካ ባሕላዊ ፌስቲቫል 2022