የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 በየአመቱ በአለም ዙሪያ የሚከበር ሲሆን አላማውም የተለየ ስልጣን እና ቦታ የሌላቸው ሴቶች ለመብቶቻቸው መከበር የከፈሉትን መሰዋትነት ፤ ያሳለፉትን ትግል እና ያስመዘገቡትን ውጤት ለመዘከር ነው።ሴቶች በትግላቸውም አንጻራዊ የሆኑ መብቶቻቸውን ለማስከበር ፤ ሰርተው ለመግባት የእድል በሮች የተከፈቱላቸው ቢሆንም በተቃራኒውም ሴቶች ዛሬም ድረስ በየትኛውም የአለማችን ክፍል ቢኖሩ የጾታ እኩልነታቸው አልተረጋገጠም።ዘንደሮም የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ሲከበር በመርህ ደረጃ የሚያጎላው የጾታ እኩልነትን ነው። የዛሬውን የውይይት መድረክ ፕሮግራማችንን ማርች 8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለመዘከር ይሆን ዘንድ ብለናል።የውይይታችን ተሳታፌዎች :- ወ/ሮ ብርቱካን ሽታዬ ቢያድግልኝ በቢሮ ኦፍ ሚቲሪዮሎጂ ክላይሜት ስፓሻል ዳታ የቡድን መሪ እንዲሁም በጂ ፒ ኤስ ሚቲሪዮሎጂ ተመራማሪ እንዲሁም ወ/ሮ እመቤት ታደሰ በናሽናል አውስትራሊያ ባንክ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አማካሪ ናቸው። በመላው አለም ለሚገኙ ሴቶች እና ለሴቶች እኩልነት ተቆርቋሪ ወንዶች ሁሉ “ መልካም የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 ” ይሁን ::
የውይይት መድረክ “ የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8” - ክፍል አንድ
LR: Embet and Bertukan Source: SBS Amharic