ለማ ክብረት ከትውልድ ቀዬው ሠንጋ ተራ ተነስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶችና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋና ግብ ጠባቂ እስከ መሆን ደርሷል። ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳትፎና ድሎች ሁነኛ ሚናዎች አበርክቷል። ክህሎቱም ለገነነ ዝና አብቅቶታል።በክፍል አንድ የግለ - ሕይወት ትረካው ከታዳጊ ቡድን ለብሔራዊ ቡድን እንደምን ለመመመረጥና መሰለፍ እንደበቃ ያወጋል።
ለማ ክብረት - ከሠንጋ ተራ እስከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
በ1975 ለማ ክብረት የሞሪሽየስን ፍጹም ቅጣት ምት አድኖ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለድል እንዲበቃ በማድረጉ ተጫዋቾች ተሸክመው (ግራ)፣ ለማ ክብረት አውስትራሊያ (ቀኝ) Source: Supplied