"የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ተደራዳሪ ሆኖ ይቅረብ ማለት የክህደትም ክህደት ነው" ደጀን የማነ
ዶ/ር ላይችሉህ ባንቴ፤ በደቡብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ የመድኃኒት ጥናትና ግኝት ተመራማሪና ደጀን የማነ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩኒቨርሲቲ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ የውይይት መድረካችን ተሳታፊዎች ናቸው። የውይይት አጀንዳዎቻችን የአገራዊ ምክክር አሥፈላጊነትና ፋይዳዎች፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ ከግጭት የመታቀብ ስምምነትና በሩስያና ዩክሬይን የመረረ ጦርነት ውስጥ ሆኖ የተኩስ ማቆም ድርድር ጥረቶች ተምሳሌነቶች ናቸው። ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
አንኳሮች
- ጊዜያዊ የግጭት ዕቀባ
- ዓለም አቀፍ አደራዳሪ አካላት
- ቀጣናዊ ግጭት