ቅዳሜ ሜይ 21 / ግንቦት 13 የሚካሔደው የአውስትራሊያ ብሔራዊ ምርጫ የውይይት መድረክ አጀንዳችን ነው። የውይይቱ ተሳታፊዎች ነርስ ኤልሳ ወልዱ - ዩናይትድ አውስትራሊያ ፓርቲን በመደገፍ፣ አቶ አበበ መኮንን - የአውስትራሊያ ግሪንስ ፓርቲን በመደገፍ፣ አቶ አያሌው ሁንዴሳ - የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲን በመደገፍ ድምፃቸውን ይሰጣሉ። ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያንም ለቤተሰብ፣ ለማኅበረሰብና ለአገር ጥቅም ሲሉ ለሚደግፏቸው ፓርቲዎች ድምፃቸውን እንዲሰጡ ይጠይቃሉ። የአውስትራሊያ ሊብራል ፓርቲን በመወከል ተጋብዘው የነበሩ ተሳታፊ በውይይቱ ወቅት አልተገኙም።
ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
ብሔራዊ ምርጫ 2022፤ የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውን ድምፆች
From L-R PM Scott Morrison (Liberal), Opposition Leader, Anthony Albanese (Labor), Greens Leader, Adam Bandt (Greens), and UAP Leader Clive Palmer (UAP). Source: Getty