ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለእገታ ከተዳረጉት ውስጥ 13 ሴቶችና 8 ወንዶች እንዲለቀቁ መደረጉንና አንድ የአካባቢውን ተማሪ አክሎ ስድስት ተማሪዎች ገና ያልተለቀቁ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ልጆቻቸው ከታገዱባቸው ወላጆች ውስጥ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ባዮ ቴክኖሎጂ ሶስተኛ አመት ተማሪዋ ግርማነሽ አባት አቶ የኔነህ አዱኛ አንዱ ናቸው። የታጋች ተማሪዎች የመለቀቅ ዜና ስላሳደረባቸው ደስታና በእገታው ወቅት ታውኮ ስለነበረ ስሜታቸው ይናገራሉ።
“ታጋች ተማሪዎች በመለቀቃቸው ደስታ ላይ ነን፤ የልጄን ድምፅ ገና አልሰማሁም” - አቶ የኔነህ አዱኛ
Source: Courtesy of DDU