ይህ የጃንዋሪ 10, 2022 የኮሮናቫይረስ በአውስትራሊያ አዲስ መረጃ ነው
- የትምህርት ቤቶች መከፈት እየተቃረበ እንደመምጣቱ መጠን ፤ እድሜያቸው ከ 5- 11 የሆኑ ሕጻናት ከአሁን ጀምሮ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ይችላሉ።
- ሌተናንት ጀነራል ጆን ፍሪወን እንዳሉት ከሉት 10,000 የክትባት መስጫዎች ውስጥ አብዛኞቹ ለህጻናቱ ክትባቱን መስጠት የሚችሉ ናቸው ፤ ወላጆች ይህንን በመገንዘብ ቀጠሮዎች በሙሉ ላይገኙ ይችላሉ ብሎ ከመገመት በተደጋጋሚ መሞከር ይኖርባቸዋል።
- ስኮት ሞሪሰን አዲስ መመሪያ ይፋ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን ፤ በተለይም አስፈላጊ በሚባሉ የሰራ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች የቅርብ ንክኪ ቢኖራቸውም ፤ ሙሉ ለሙሉ ከተከተቡ እና የኮቪድ-19 ምልክቶችን እስካላሳዩ ድረስ ራሳቸውን ለይቶ ማቆየት አይጠበቅባቸውም ።
- በኩዊንስላድ ተማሪዎች በፌብሩዋሪ 7 ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ቀድሞ ታቅዶ ከነበረው ጃንዋሪ 24 በሁለላት ሳምንት ዘግይቶ ነው ።
- በኒው ሳውዝ ዌልስ 2,030 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ፤ ከነዚህም መካከል እሁድ ይፋ ከሆነው ቁጥር 1,927 የሚሆኑት ውስጥ159 ያህሉ ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያስፈልገበት ክፍል የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ 151 በዚሁ ይገኛሉ ።
- በቪክቶሪያ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሆስፒታል የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ከ752 ወደ 818 ከፍ ብሎ አድሯል ።
- በኩዊንስላድ 419 ሰዎች በሆስፒታል ክትትል የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህ መካከልም 21 የሚሆኑት ከፍተኛ እንክብካቤ በሚያስፈልገበት ክፍል የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት 7ቱ የመተንፋሻ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ።
- በቪክቶሪያ ሶስተኛው የኮቪድ-19 ክትባት በተወሰኑ የስራ መስኮች ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች ግዴታ እንደሚሆን የጤና ሚኒስትሩ ማርቲን ፎሌይ አስታውቀዋል ።
- የኒው ሳውዝ ዌልስ ፕሪምየር ዶሚኒክ ፔሮቴት ተጨማሪ 50 ሚሊየን ፈጣን የመመርመሪያ ቁሳቁሶችን ማዘዛቸውን ያሳወቁ ሲሆን ፤ ይህም የክለሉን አጠቃላይ ቁጥር ወደ 100 ሚሊዮን ከፍ ያደርገዋል ።
- የኒው ሳውዝ ዌልስ መንግስት በፈጣን መመርመሪያዎች የሚገኙ ወጤቶች ከያዝነው ሳምንት ጀምሮ ኒው ሳውዝ ዌልስ ሰርቪስ አፕ እንደሚመዘገብ ይፋ አድርጓል
- አብዛኛዎቹ ክልሎችም በፈጣን መመርመሪያ የሚገኙ ውጤቶችን የሚመዘግቡበት ቅጾችን አዘጋጅተዋል ።
የኮቪድ -19 አሀዛዊ መረጃዎች
ኒው ሳውዝ ዌልስ በፒ ሲ አር በተመረመረ ምርመራ 20,239 በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን 18 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ። ኒው ሳውዝ ዌልስ በፈጣን መመርመሪያ የሚገኙ ውጤቶችን ገና መመዝገብ አልጀመረችም ።
ቪክቶሪያ 34,808 ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሁለት ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል ።
ኩዊንስላድ ቢያንስ 9,581 ሰዎች መያዛቸውን ያስታወቀች ሲሆን ባለስልጣናቱ የተቀሩትን በ ፒ ሲ አር እና በፈጣን መመርመሪያዎች የተወሰዱትን ወጤቶች በመቁጠር ላይ ናቸው ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 939 አዲስ ተያዦችን ያስመዘገበ ሲሆን በታዝማንያም 1,218 ሰዎች ተይዘዋል ።
በክልልዎ ኮቪድ-19ን በተመለከተ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በቋንቋዎ ማግኘት ካሻዎ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ here.
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
Find out what you can and can't do in your state or territory
ጉዞ
Information for international travellers and የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ in language
የገንዘብ እርዳታ
የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ከ 70 እና 80 በላይ ከሆነ ጀምሮ የክፍለ ሀገሮች የኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ ክፍያ ህጎች ተለውጠዋል
- ዜናዎችን እና መረጃዎችን ከ 60 በላይ ቋንቋዎች ከ sbs.com.au/coronavirus
- የየክፍላተ ሀገራቱን መረጃ በተመለከተ ፦ NSW, Victoria, Queensland, Western Australia, South Australia, Northern Territory, ACT, Tasmania.
- የኮቪድ-19 ክትባትን በቋንቁዎ መረጃን በተመለከተ ፦ COVID-19 vaccine in your language
- Visit the translated resources published by NSW Multicultural Health Communication Service
- COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool. - የክፍላተ ሀገራቱን የመመርመሪያ ክሊኒኮች
- NSW
- Victoria
Queensland
South Australia
ACT
Western Australia
Tasmania
Northern Territory
iframe src="https://www.sbs.com.au/labsembeds/vaccinated-dashboard-naca/index.html" data-module="iframe-resize_module"]