Coming Up Fri 10:00 PM  AEDT
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio

ኮቪድ-19 ምልክቶችን ሳያሳይ መተላለፉ ምን ያህል ተለምዶአዊ ነው ሊያስጨንቀንስ ይገባል?

Source: Getty Images

ኮቪድ- 19 ምልክቶችን ሳያሳይ መተላለፉ ምን ያህል ተለምዶአዊ ነውሊያስጨንቀንስ ይገባል?

ስለኮቪድ- 19  ብዙ ከመስማታችን የተነሳ ምልክቱን በተመለከተ ብዙዎቻችን ከክፍተኛው ትኩሳት እስከ ደረቅ ሳል ፤ ከመተንፈስ ማቃት እስክ ከባድ ድካም የሚሉትን በቀላሉ ለማወቅ ችለናል፡፡

ይሁንና እንደ አይስላንድ ፤ ጃፓን፤ቻይና ፤ እና አውስትራሊያን ያሉ አገራት ባደረጉዋቸው ጥናቶች መሰረት ምንም አይነት ምልክትን ያላሳዩ የኮቪድ- 19 ህመምቶኞችን ማግኘታችውን ነው፡፡

ጃማ ኒትወርን የተሰኘው ይፋዊ የጥናት ወረቀት ባወጣው መረጃ መሰረት በቻይና 78 ከሚሆኑት ህሙማን 42.3 በመቶ ያህሉ ምንም አይነት ምልክቶችን አላሳዩም፡፡

ሌላኛው እና በአውስትራሊያውያን ተመራማሪዎች ለህትመት የበቃው ቶራክስ ግኝት መሰረትም በግሬግ ሞርቲመር የክሩዝ መርከብ ላይ ከነበሩት 217 ተሳፋሪዎች መካከል ከ10 ሰዎች ውስጥ ከስምት በላይ የሚሆኑት እና በምርመራ የኮቪድ- 19 የተኘባችው ስዎች ምንም አይነት ስሜቶችን ያላሳዩ ነበሩ፡፡

ቻይና 1300 የሚሆኑ ምንም አይነት ምልክቶችን  ያላሳዩ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ማግኛቷንም ይፋ አድርጋለች፡፡

ቅድሚያ ምልክቶች በማሳየት እና ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳዩ የሚተላለፉትየትኞቹ ናቸው?

የአለማቀፉ የጤና ድርጅት በሁለቱ መካከል ያለውን ይፋ አድርጓል

ቅድሚያ ምልክቶች የሚባለው ጊዜ ለቫይረሱ ከተጋለጡ በኋላ ኝ ደግሞ የቫይረሱ ምልክቶች ሳያሳዩ የሚቆዩበት ጊዜ ነው፡፡ይሁንና ምንም ምልክቶች ባይታይም ማስተላለፍ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡በርከት ያሉ ጥናቶችም እንዳሳዩትም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከአንድ እስክ ሶስት ቀናት ድረስ ምልክቶችን ሳያሳዩ ሊቆዩ እንደሚቸሉ ነው፡፡

ምልክት ሳይታይ ቫይረሱን ማስተላለፉ ሲባልም በኮቪድ- 19 የተያዘ  ሰው ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ ለሌሎች የማስተላለፍብት ሂደት ነው፡፡

ባለሙያዎቹ በቅርቡ ስለወጣው የጥናት ውጤት ምን ያስባሉ ?

በኪምበርሊ ኢንስቲትዩት የባዮሴኪዩሪቲ ፕሮግራም ሃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ራይና ማክኢንታየር ፤ ኮቪድ - 19 ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ወይም ቅድመ ምልክቶችን በማሳየትን ሊከሰት እንደሚችል ተለምዶአዊ መሆኑን የሚያመላክቱ  በቂ የሆኑ መረጃዎች አሉን ብለዎል፡፡

ለዚሀም በማሳያነት የጠቀሱት በአረጋውያን ማቆያ ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ወረርሽኝ ተከተሎ የተደርገውን ጥናት ሲሆን ፤ ምርመራ ከተደረገላቸው 50 በመቶ እና ከዚያም በላይ ያህሉ ሰዎች ምንም አይነት ምልክትን ያላሳዩ ነበሩ፡፡

በሜይ ወር መጀመሪያም በቦካሽ ማርሽ በሚገኝ ግራንት ሎጅ የአረጋውያን መጦሪያ የሚሰራ አንድ ግለሰብ ምንም ምልክቶችን ሳያሳይ ቫይረሱ ተገኝቶበታል፡፡

“ ከዚሀ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ መከራከር የለብንም ፤ ወረርሽኝ በሚከሰት ጊዜም በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑትን የቤተሰብ አባላትንም ሆነ የቅርብ ንክኪ ያላቸውን በሙሉ ምልክቱን ቢያሳዩም ባያሳዩም ምርመራውን ማድረግ ይኖርብናል   ያለበለዚያ በወቅቱ ማግኘት የሚገባንን መረጃዎች እናጣለን ፡፡  “ ብለዋል ፕሮፌሰር ማክኢንታየር

“ ሰዎች የሰውነታቸውን መከላከያ ለማዳበር ከ 10-14 ቀን ሊፈጅባቸው ይችላል ፤ ስለሆነም በነዚህ ጊዜያት ውስጥ የሚደረግ የሰውነት መከላከያን መሰረት ያደረገ ፈጣን ምርመራ ዉሱን መሆን ብዙም ላያስደንቅ ይችላል ፡፡ “

አንዳንድ ተንታኞችም ምልክት የማያሳየውን የኮቪድ- 19 ባህሪ በተመለከት እርግጠኖች አለመሆናቸውንም ይናገራሉ፡፡

ሳንጄይ ሴናያካ በአውስትራሊያ ናሽናን ዩኒቨሪሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ልዩ ሃኪም ፤ በቻይና የተደረገውን ጥናት እና ጸሃፊው የደመደመበትን ሃሳብ መሰረት አድርገው ሲናገሩ ፤ ምልክቱን ያላሳዩት ሰዎች ምናልባትም ራሳቸውን ለይተው ያላቆዩ ይሆናል፤ በነሱም ሳቢያ የተከሰተ ቫይረስ መኖሩም አልታየ ይሆናል ለዚህ ምክንያቱም ራሳቸውን አግልለው መቀመጣቸው ነው ብለዎል፡፡

በፌብሩዋሪ ወር የአለም የጤና ድርጅት ከቻይና ጋር በጣምራ ባወጣው ዘገባ መሰረት በምርመራ ወቅት ምንም አይነት ምልክቶችን ያላሳዩ ሰዎች ቆይተው ምልክቶችን አሳይተዎል ብሏል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ሴናያካ እይታ ከሆነ  በጥናቱ ላይ የተካተቱት ህመምተኞች ከታመሙ በኋላ መሄዳቸውንም ሆነ አለመሄዳቸውን በተመለከት ግልጽ አይደለም የሆነ መረጃ አልቀረበም፡፡

የጥናቱን ግልጽ ያለመሆንን በተመለከት ያነሱት ነጥብ ጸሃፊውም የተቀበለው ነው፡፡ይህውም ምንም አይነት ምልክት ያላሳዩት  የምርመራ ውጤቶች ምን ያህል እርግጠኝነት አላቸው የሚለውን ነው፡፡  ምናልባትም በጣም አልታመሙ ይሆናል በአንጻሩ ደግሞ 100 በ መቶ ጤንነት የማይሰማቸው ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ሲያርፉበት ጥሩ ሊሰማቸው ይችላል ነገር ግን ውጭ ወጥቶ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን መስራት አይችሉ ይሆናል፡፡

በአንጻሩ አይስላንድ 50 በመቶ የሚሆኑት በኮቪድ-19 የተያዙት ስዎች ምንም አይነት ምልክቶችን ያላሳዩ ነበሩ ብላለች፡፡ በጃፓን 38.8 በመቶ የሚሆኑት ታማሚዎች እንዲሁ ምልክቶችን ያላሳዩ ሲሆኑ በቻይና በተደረገ ሌላ ጥናት ቁጥሩን ወደ 80 በመቶ ከፍ አድርጎታል፡፡

“ የትኛው መረጃ ትክክለኛ እንደሆነ ለማወቅ ይከብዳል ይሁንናና ምልክቶችን ሳያሳይ የሚከሰተውን የኮቪድ-19 መጠን ለመረዳት የቀረን ጥቂት ነው፡፡ አሁንም ድርስ እርግጠኛ ያልሆንነው ተለይተው ሳይታወቁ ምን ያህል ለሌሎች ሊያስተላለፉ እንደሚቸሉ ነው::

በሌላ አባባል ከእያንዳንዱ ታማሚ ጀርባ ሌሎች አራት የሚሆኑ እና ምንም አይነት ምልክቶችን ያላሳዩ ቫይረሱ የነበረባቸው ሰዎች ወይም ተሸካሚዎች አሉ ማለት ነው፡፡

ፕሮፌሰር ኢቮ ሙለር በዋልተር እና ኤላይዛ ሆል ኢኒስቲትዩት ኦፍ ሜዲካል ሪሰርች  የተላላፊ በሽታዎች ተመራማሪ እንደሚያስረዱት ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳዩ ኮቪድ-19ን ማስተላለፋፍ የሚቻል መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚቻል ማወቅ ብቻ አይደለም ግባችን ፤ ከዚህ ባሻገርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመጬዎቹ ወራቶች እንዴት ሊከሰት ይችላል የሚለው ግምታችንም ላይ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

“ ስለሆነም ቅድመ ጥንቅቄን መውሰድ በሁለተኛው ዙር ሊከሰት የሚችለውን የሞት አደጋ ላመከላከል  አይነተኛው መንገድ ነው ፡፡” ብለዋል

በግሬግ ሞንቲመር ክሩዝ መርከብ ለይ በተደርገው ጥናት መሰረት ክ217 ተሳፋሪዎች  መካከል 96 አውስትራሊያውያን  ነበሩ፡፡ በሁሉም ተሳፋሪዎች ላይ በተደረገው የምርመራ ውጤትም 128 ያህሉ ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል ፡፡ከነዚህም መካከል 104 ይህሉ ምንም አይነት ምልክቶችን ያላሳዩ ሲሆን ቀሪዎቹ 81 በመቶ ያህሉ ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል፡፡

“ በሌላ አባባል ከእያንዳንዱ ታማሚ ጀርባ ምንም አይነት ምልክቶችን ያላሳዩ እና ቫይረሱ የነበረባቸው አራት ሰዎች አሉ ማለት ነው፡፡በተመሳሳይ አካሄድ በሌሎች ቦታዎችም የሚታየው ይህው ነው፡፡ይህ ማለትም ምልክቶችን ያሳዩ ስዎችን ብቻ የሚመረምሩ አገራት የሚያገኙዋቸው አሃዛዊ መረጃዎች ትክክለኛውን ቁጥር የማያሳይ ሲሆን ውጤቱም ከአምስት እጥፍ በላይ እንደሚሆን ነው፡፡”

ፕሮፌሰር ሙለር እንደሚሉት ከሆነ “ በየትኛውም እድሜ ውስጥ ያሉት እና ምንም ምልክትን ሳያሳዩ ለሌለው ሊያስተላልፉ የሚችሉ የቫይረሱን ተሸካሚዎችን መለየት አፋጣኝ እና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር መሆን አለበት፡፡”

በአውስትራሊያ የሚኖሩ ዜጎች 1. 5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው፡፡ መሰባሰብን በተመለከተም የክልሉን ገደብ መመልከት ያስፈልጋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በአሁን ሰአት በሰፊው ይደረጋል፡፡የብርድ ወይም ጉንፋን ምልክቶችን ካሳዮ ሃኪምዎ ጋር በመደወል ምርመራን እንዲያደርጉ መጠየቅ የሚችሉ  ሲሆን ወይም coronavirus Health Information Hotline on 1800 020 080 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

The federal Government’s coronavirus tracing app COVIDSafe በይፋ ስለወጣ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፡

ኤስ ቢ ኤስ ለአውስትራሊያውያን መድብለ ባህል ማህበረሰብ አዳዲስ ኮቪድ- 19 መረጃዎችን በትጋት ያደርሳል፡፡ ዜናዎች እና መረጃዎች በ63 ቋንቋዎች ይገኛሉ ከwww.sbs.com.au/coronavirus