Coming Up Fri 10:00 PM  AEST
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio

ኮቪድ-19 ፡ ምልክቶቹ ፤ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት እና ማህበረሰባዊ ርቀት

Woman in quarantine Source: Getty Images/Jasmin Merdan

SBS በቋንቋዎ ስለ ኮቪድ - 19 ወረርሽኝ የተጣሩ ዘገባዎችን ያለማቋረጥ ሊያቀርብልዎ ተነስቷል። ይህ መዘርዝረ ጭብጥ እያንዳንዱ ማኅበረሰብ ሊያውቀው የሚገባውን መረጃ አካቷል።

በቤትዎ ውስጥ ይቆዩ  ተጠብቀው ይቆዪ የሌሎችንም ህይወት ያትርፉ

SBS COVID-19 የየክልሎችን መረጃ በተመለከተ ፦  CLICK HERE

 የገንዘብ ችግሮች

" የገንዘብ ችግር ካጋጠመዎት የሚከተለውን ድረገጽ  www.moneysmart.gov.au ይመልከቱ ወይም የብሄራዊ የእዳ መርጃ መስመር ላይ 1800 007 007 ይደውሉ ፡፡

በወረርሽኝ ወቅት ለሚወስድ እረፍት የሚከፈል የድንገተኛ ጊዜ ክፍያ

 • የማእካላዊ መንግስት የ$1500 "የድንገተኛ ጊዜ ክፍያን" ያስተዋወቀ ሲሆን ሰራተኞች ነሆኑ እና በቪክቶርያ ፤ ታዝማንያ ፤ ዌስተርን አውስትራሊያ ፤ እንዲሁም በቅርቡ ከሴፕቴምበር እስክ ኦችቶበር ባለው ጊዜ ውስጥ ኒው በሳውዝ ዌልስ  የሚኖሩ ሁሉ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡
 • ኩዊንስላንድ ከማእከላዊ መንግስቱ ጋር ስምምነትን በማድረግ ላይ ያለች ሲሆን በቅርቡም እንደምትቀላቀል ይጠበቃል ፡፡
 • ክፍያው እንዲያመለክቱ የሚፈቀድላቸው ራሳቸው ለይተው ማቆየት ያለባቸው እና በቂ የህመም ጊዜ ፍቃድ የሌላቸው እንዲሁም የስራ ፈላጊዎችም ሆነ የስራ ማቆያ ክፍያ የሌላቸው ሰራተኞች ብቻ ናቸው፡፡ 

የስራ ፈላጊዎች እና ስራን የሚየቆይ ክፍያዎች ( Jobseeker and Job Keeper payments )

እነዚህ ክፍያዎች እስከ 21 ማርች 21, 2021 ድረስ እንዲቆዩ የተራዘሙ ሲሆን መጠናቸው ግን ከሴፕቴምበር 2020 ጀምሮ ይቀንሳል፡፡

የስራ ፈላጊዎች ክፍያ  ፦ ( Jobseeker )

የስራ ፈላጊዎች ክፍያ እድሜያቸው  ከ 22 አመት ጀምሮ እስክ ጡረታ ድረስ ላሉ የሚከፈል ሲሆን ፤ ስራ አጥ ሆነው ወይም  ስራን በመፈለግ ላይ ካሉ ወይም የተረጋገጠ ስልጠናን እያከናወኑ ከሆነ ክፍያውን ማግኘት ይችላሉ ፡፡

 • በአሁን ሰአት ያለው የክፍያ መጠን ፦  $1,115
 • ከሴፕቴምበር 2020 ጀምሮ የሚኖረው የክፍያ መጠን ፦  $815

በተጨማሪም ከሴፕቴምበር ጀምሮ ከስራ ቦታዎ በየሁለት ሳምንቱ እስከ $300 ያህል ድረስ ክፍያዎ ሳይነካ መስራት ይችላሉሉ፡፡ በአሁን ሰአት ያለው ገደብ $ 106 ነው፡፡

ማንኛውም የስራ ፈላጊ ክፍያውን በቀጣይነት ለመቀበል ከኦግስት 4 ጀምሮ ከስራ አፈላላጊ ድርጅቶች ጋር የመገናኘት ግዴታ ያለበት ሲሆን በየወሩም አራት ስራዎችን መፈለግ ይኖርበታል፡፡

ስራን የሚያቆይ ክፍያ ፦ ( Job Keeper )

ስራን የሚያቆይ ክፍያን የሚያገኙት እድሜያቸው ከ 16 አመት በላይ የሆኑ እና በ ማርች 1፤ 2020 የግል ተቀጣሪዎች የሆኑ ፤ የሙሉ ጊዜ እና የጊዜያዊ ተቀጣሪዎች ወይም ጊዜያዊ ስራን ቢያንስ ለ 12 ወራት እና ከዚያ በላይ የሰሩ ለክፍያው ማመልከት ይችላሉ ፡፡ እድሜያቸው 16 እና 17 የሆኑት ክፍያን በማግኘት ራሳቸውን ሲያስተዳደሩ እንደቆዩ ማሳያን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡

ይህ ክፍያ  ለሙሉ ጊዜ እና ለትርፍ ጊዜ ሰራተኞች በሚል  " በሁለት ደረጃዎች " ተከፍሏል ፡፡

የሙሉ ጊዜ ሰራተኞች የሁለት ሳምንት ክፍያዎች ፦

 • በአሁን ሰአት ፦ $1,500
 • ከሴፕቴምበር ጀምሮ ፦ $1,200
 • ከጃንዋሪ ጅምሮ ፦ $1,000

ለትርፍ ጊዜ ሰራተኞች

 • በአሁን ሰአት ፦ $1,500
 • ከሴፕቴምበር 2020 ጀምሮ ፦ $750
 • ከጃንዋሪ 2021 ጅምሮ ፦ $ 650

ኮቪድ - 19 የሚዛመተው እንደምን ነው?

ኮቪድ - 19 ከሰው - ወደ - ሰው የሚዛመተው፦

 • በቫይረሱ ተጠቅቶ ካለ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ወይም በቫይረሱ የመያዙ ምልክት በግልፅ ከመታወቁ 24 ሰዓታት በፊት በቅርበት የተገናኙ ሲሆን

 • በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሆኖ ከሚያስል ወይም ከሚያስነጥስ ሰው ጋር በቅርበት የተገናኙ እንደሁ

 • በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሳል ወይም ንጥሻ የበከላቸውን ቁሶች ወይም ጠርዞች (እንደ የበር እጀታዎች ወይም ጠረጴዛዎች) ነክተው አፍዎን ወይም ፊትዎን የነኩ እንደሆነ 

 • የአውስትራሊያ መንግስት ሁሉም ነዋሪዎች የኮቪድሴፍ አፕን እንዲጭኑ ምክሩን ይለግሳል፡፡ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ድረ ገዕ ይመልከቱ፦

https://www.sbs.com.au/language/english/australia-launched-covidsafe-a-coronavirus-contact-tracing-app

የኮቪድ - 19 ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች የፌዴራል መንግሥቱ ድረ-ገፅ እንደሚያመለክተው ከአነስተኛ ሕመም እስከ የሳምባ ምች የሚደርስ ዘርፍ አላቸው።

የኮቪድ - 19 ምልክቶች ከጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ ጋር ተመሳሳይነት አለው።

እነሱም፡

 • ትኩሳት

 • የመተንፈሻ አካል ህመም

 • ሳል

 • የጉሮሮ መከርከር

 • የትንፋሽ መቆራረጥ

 • ሌሎች ምልክቶች የአፍንጫ ፈሳሽ ፤ራስ ምታት ፤ የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመም ፤ ማቅለሽለሽ ፤ ተቅማጥ ፤ ማስመለስ ፤ የማሽተት ስሜትን ማጣት ፤ የማጣጣም ስሜት መቀየር ፤ የምግብ ፍላጎትን ማጣት እና ድካም ይገኙበታል፡፡

በመስኩ የተሰማሩት ባለሙያዎች የኮቪድ 19 ምልክቶች ሲታዩ በቤታችን ሆነን እንዴት መለየት እንደሚችል የሚረዳ መንግድን አዘጋጅተዋል፡፡

https://www.healthdirect.gov.au/symptom-checker/tool/basic-details

ምልክቶቹ ከታዩብኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

ከባሕር ማዶ ወደ አውስትራሊያ በተመለሱ 14 ቀናት ውስጥ ወይም  በኮቪድ - 19 መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ከተገናኙ በኋላ ምልክቶቹ ከታየብዎት ለአስቸኳይ ምርመራ ሐኪምዎን በፍጥነት ለማየት ቀጠሮ ማመቻቸት ይኖርብዎታል።

ቀጠሮ ለማስያዝ ሐኪምዎ ዘንድ ይደውሉ ወይም የብሔራዊ ኮሮናቫይረስ የጤና መረጃን በቀጥታ ስልኩ 1800 020 080 ደውለው ያነጋግሩ። ምልክቶቹ ያለብዎት መሆኑን ሳይገልጡ ወደ ጤና ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል አይሂዱ።

ወደ ጤና ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል ከመሔድዎ በፊት የጉዞ ታሪክዎን ወይም  በኮቪድ - 19 መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር የተገናኙ መሆንዎን ሊነግሯቸው ይገባል። የሕዝብ ጤና ባለ ሥልጣናት ወደ ቀድሞ አዘቦታዊ እንቅስቃሴዎችዎ መመለስ ይችላሉ ብለው ይሁንታቸውን እስካልሰጥዎት ድረስ በቤት፥ ሆቴል ወይም የጤና ክብካቤ ክፍሎች ውስጥ ራስዎን አግልለው ሊቆዩ ይገባዎታል።

መተንፈስ ከተቸገሩ ወይም ድንገተኛ የሕክምና አደጋ ከገጠመዎ 000 ይደውሉ።

የሚሰማዎትን ምልክቶች በተመለከት ከባለሙያዎች ጋር መነጋገር ካስፈለገዎ የብሄራዊ ኮሮና ቫይረስ ልዩ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ምክርን ይጠይቁ።የስልክ መስመሩም ለ24 ሰአት በሳምንት ሰባቱንም ቀን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ቁጥሩም  1800 020 080

በክልልዎ ወይም ግዛትዎ  GP respiratory clinic  መኖራቸውን ለማረጋገጥ እና  ቀጠሮ ለመያዝ እና እንዴት መመዝገብ እንዳለብዎ ለማረጋገጥ ይሞክሩ

በአካባቢዎ ከሌለም የጤና ሃላፊዎችን ውይም የግዛቱን የጤና ማእከል ድረ ገዕ ይጎብኙ፡፡ የትኩሳት መመርመሪያ ክሊኒኮችን ሌሎች አገልግሎቶች በተመለከተ የክልሉን እና ግዛቱን የጤና ማእከል ድረ ገዕ ይመልከቱ ( state or territory health department website

የመተንፈስ ችግር ወይም ድንገተኛ የጤና ችግር ከገጠመዎ 000  ይደውሉ፡ 

ለብርቱ በሽታ የተጋለጡት እነማን ናቸው?

የተወሰኑ ሰዎች ለሕመም ተጋልጠው ሕመም ላያድርባቸው ይችላል፥ የተወሰኑቱ መለስተኛ የሕመም ምልክቶች አሳይተው በቀላሉ ይድናሉ፥ ሌሎች ግና በአጭር ጊዜ ውስጥ በጣሙን ለመታመም ይበቃሉ። ካለፉት ተሞክሮዎች በአብዛኛው ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ፦

 • አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ስር የሰደዱ ሕመሞች ያሉባቸው እድሜያቸው ከ 50 አመት በላይ የሆኑ ነባር ዜጎች እና ቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ፤ 

 • እድሜያቸው ከ 65 አመት በላይ የሆኑና ስር የሰደዱ ሕመም ያሉባቸው ሰዎች ፡፡

 • እድሜያቸው ከ 70 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች

 • የሰውነት መከላከያ አቅማቸው የተደከመ ሰዎች ናቸው፡፡

 ኮቪድ-19 እንዳይስፋፋ እርስዎ እንደምን ሊያግዙ ይችላሉ?

ሲያስነጥሱና ሲያስሉ በእጅዎ መሸፈንና ታመው ሳሉም ከሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በአብዛኛው  ከበርካታ ቫይረስ ማለፊያ መከላከያ ነው። ሊያደርጉ የሚገባዎት፤

 • ከቤትዎ የግድ ሊያስወጣዎ የሚችል ምክንያት ካልገጠምዎት አይውጡ

 • የ1.5 ሜትር ማኅበራዊ ርቀትን ይጠብቁ እንዲሁም 1 ሰው በ 4 ስኩየር ሜትር ደንብን ይተግብሩ

 • እጆችዎን አዘውትረው በሳሙናና በውኃ ይታጠቡ፤ ምግብ ከመመገብዎ በፊትና ተመግበው ሲያበቁ፤ እንዲሁም መፀዳጃ ቤት ከተፀዳዱ በኋላ ይታጠቡ 

 • ሳልዎንና ንጥሻዎን ይሸፍኑ፤ የመፀዳጃ ወረቀቶችንና አልኮልነት ያላቸውን የእጅ ማፅጃዎች ይጠቀሙ

 • ጤንነት ካልተሰማዎት ከሌሎች ጋር ከመገናኘት ይቆጠቡ (ከሰዎች ጋር የ1.5 ሜትሮች ርቅትን ይጠብቁ) 

 • ግላዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፤ በተቻለ መጠን ከቤትዎ አይውጡ።

ከሰዎች ተገልለው መቆየት ግድ የሚላቸው እነማን ናቸው?

ሀ)  ወደ አውስትራሊያ የመጡ ማናቸውም ሰዎች ወይም በኮቪድ-19 ከተጠቃ ሰው ጋር በቅርበት ተገናኝቻለሁ የሚል አመኔታ ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን ለ14 ቀናት አግልለው ሊቆዩ ይገባል።

ለ)  ወደ አውስትራሊያ የመጡ ማናቸውም ሰዎች በተሰናዱላቸው ለይቶ ማቆያ ሥፍራዎች (ለምሳሌ ሆቴል) ለ14 ቀናት ራሳቸውን ሊያገሉ ይገባል።

 • መንገደኞች ተገቢውን የጤና፣ ኢሚግሬሽንና የጉምሩክ ፍተሻ ካካሄዱ በኋላ በቀጥታ ወደ ተዘጋጁላቸው ለይቶ ማቆያ ሥፍራዎች ይጓጓዛሉ።

ሐ) በኮቪድ - 19 የተያዙ ከሆነ ከቤትዎ መውጣት የለብዎትም።

 • ወደ ሥራ፥ የገበያ አዳራሾች፥ ትምህርት ቤት፥ ሙዋዕለ ሕፃናት ወይም ዩኒቨርሲቲን የመሳሰሉ የሕዝብ መገኛ ሥፍራዎች እንዳይሔዱ

 • ሰዎች ምግብዎንና የሚያስፈልግዎትን ነገሮች በርዎ ላይ አስቀምጠውልዎት እንዲሔዱ ይጠይቁ

 • ሁሌም አብረዎት ከሚኖሩ ሰዎች በስተቀር ሌሎች ጎብኚዎችን ወደ ቤትዎ ፈቅደው አያስገቡ

ማኅበራዊ ርቀት 

 • ማኅበራዊ ርቀት ወይም አካላዊ መራራቅ እንደ ኮቪድ-19 የመሳሰሉ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚያግዝ አንዱ መንገድ ነው። በየጊዜው በእርስዎና በሌሎች ሰዎች መካከል ርቀቶች በተጠበቁ ቁጥር ቫይረሱ በስፋት መዛመት ይሳነዋል።

 • በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሳል ወይም ንጥሻ የበከላቸውን ቁሶች ወይም ጠርዞችን (እንደ የበር እጀታዎች ወይም ጠረጴዛዎች) ከመንካት መታቀብን ያካትታል።

አውስትራሊያውያን እጅግ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ማናቸውንም ጉዞዎች መሰረዝ ይኖረባቸዋል፡፡ክልሎች እና ግዛቶችም ክልላቸውን ለመዝጋትም ሆን ክፍት ለማድረግ የራሳችውው ውሳኔ መሳለፍ ይችላሉ፡፡

በቤትዎ ይቆዪ 

ለመላው አውስትራሊያውያን ከሄራዊ ካቢኔው የተሰጠው ጠንካራ መመሪያ የሚለውም ፤  ለአንገብጋቢ ጉዳዮች ካልሆነ በቀር በቤትዎ ይቀመጡ የሚለው ነው ፡፡እነሱም ፦

 • የሚያስፈልግዎትን ቁሳቁሶች ለመገብየት  ፤ ምግብና የአስፈላጊ ነገሮች ግብአት
 • የህክምና እና የጤና ክብካቤ ላማግኘት ፤ የተለየ ትኩረት የሚሰጥባቸውንም ጭምር
 • በህብረተሰብ ደረጃ በጋራ የመሰብሰብ ህግን ባከበር መልኩ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
 • ለትምህርት እና ለስራ ፤ እነዚህንም ከቤትዎ ሆነው ማድረግ ካልቻሉ የሚሉት ናቸው ፡፡

በአረጋውያን መጦሪያ ያሉ ቤተሰቦቼንና ጓደኞቼን መጠየቅ እችላለሁን?

እንደ አጠቃላይ ህግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሚመለከቷቸው አውስትራሊያውያን ሁሉ  ወደ አረጋውያን መጦሪያዎች ቤቶች መሄድ የለባቸውም ፦  

 • ባለፉት 14 ቀናት ከባሕር ማዶ የተመለሱ ከሆነ

 • ባለፉት 14 ቀናት በ ኮቪድ - 19 መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ተገናኝተው ከሆነ

 • ትኩሳት ወይም የመተንፈሻ አካላት ሕመም ምልክቶች ካሳዩ (ሳል፥ የጉሮሮ መከርከር፥ ሙሉ ለሙሉ መተንፈስ አለመቻል) የአረጋውያን መጦሪያዎችን አይጎብኙ።

 • ማንኛውንም የአረጋውያን መጦሪያ ቤቶችን ለመጎብኛት የኢንፍሉዌንዛ ክትባትን መውሰድ ይኖርብዎታል ፡፡

ልብ ይበሉ ክልሎች እና ግዛቶች የብሄራዊውን ካቢኔ መመሪያዎች በማይጣረስ መልኩ የራሳቸው የሆነ የተለየ መመሪያዎች አላቸው ፡፡

የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ይኖርብኛልን ?

በቅርቡ በአውስትራሊያ ማህበረሰብ ውስጥ የታየው የ COVID-19 መዛመት ያስከተለው ነገር አለ ፡፡ይህውም ክለሎች እና ግዛቶች የፊት መሸፈናኛ ጭንብልን በተመለከት ነዋሪዎች እንዲጠቀሙ ማድረግ ወይም መደረግ እንዳለብት ምክርን እየለገሱ ይገኛሉ ፡፡

እንደሚኖሩባቸው የቪክቶርያ አካባቢዎች በአሁን ወቅት የፊት መሸፈናኛ ጭንብል መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ወይም በምክር መልክ የሚቀርብ ሆኗል ፡፡ይህም የሆነው በማህበረሰብ ውስጥ የታየው የኮሮናቫይረስ ስርጭት ስለጨመረ ነው ፡፡ https://www.dhhs.vic.gov.au/face-coverings-1159pm-wednesday-22-july

በኒውሳውዝ ዌልስ የሚኖሩ እና የኮሮናቫይረስ በታየባቸው አካባቢ የሚኖሩ ወይም የሚሰሩ ሰዎች የፊት መሸፈኛ ጭንብል እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡

የፊት መሸፈኛ ጭንብል እንደተጨማሪ መከላከያ ማገልገሉ እንዳለ ሆኖ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎችን ማድረግ መቀጠል ይኖርብዎታል፦

 • ጤንነት ካልተሰማዎ ከቤትዎ አይውጡ 
 • አካላዊ ርቀትን ይጠብቁ ( ከ1.5 ሜትር በላይ ) ከሌሎች ሰዎች ዘንድ ይራቁ 
 • በርካታ ሰዎች የተሰባሰቡበት ቦታዎች ከመሄድ ይቆጠቡ
 • የእጅ እና የመተንፈሻ አካላት ንጽህና ልምምዶችን ያድርጉ ፡፡

በሚኖሩበት ክልል እና ግዛቶች የፊት መሸፈኛ ጭምብልን በተመለከተ የሚወጡት መመሪያዎች ሊቀያየሩ ስለሚችል ወቀታዊ መረጃዎችን መከታተል ያስፈልጋል፡፡

ከአውስትራሊያ ፤ ወደ አውስትራሊያ ወይም በአውስትራሊያ ውስጥ የሚደረጉ ጉዞዎችን በተመለከተ 

አውስትራሊያውያን አስፈላጊ ከሆኑት ውጭ ማንኛውንም የአገር ውስጥ ጉዞዎች ማስወገድ ይኖርባቸዋል ፡፡ክልሎች እና ግዛቶች የራሳቸን የገደብ ህጎች እስከ ድንበሮችን መዝጋት ደረስ በተግባር ማዋል ይችላሉ ፡፡

በግዴታ የሚደረጉ የመረጃ ስብሰባዎች

ከኦክቶበር 1 ፡ 2020 ጀምሮ በአገር ውስጥ በረራ የሚገቡ ሁሉ ስማቸውን ፤ የኢሜል አድራሻቸውን ፤ የሞባይል ቁጥራቸውን እና የሚኖሩበትን ከተማ የማሳወቅ ግዴታ ይኖርባቸዋል ፡፡ይህ መረጃ ሊኖሩ የሚችሉ የኮሮናቫይረስ ንክኪዎችን ተከታትሎ ለመያዝ የሚረዳ ነው፡፡

የአዳሪ ትምህርት ቤቶች

በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ከሴፕቴምበር እስከ ኦክቶበር ባለው የእረፍት ጊዜ ውስጥ ውስጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ ይችላሉ ፡፡በተለይ ከከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ተማሪዎች፡፡

የህዝብ መጓጓዣዎች መሰረታዊ ደንቦች

የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች በክለሎች እና ግዛቶች አስተዳዳሪዎች የሚመሩ ሲሆን የብሄራዊ የካቢኔ አባለት ጠንካራ የሆኑ ደቦችን ያወጣሉ፡፡ ይሀውም የሰራተኞችን ጤና እና ደህንነት እንዲሁም የተሳፋሪዎችን ደህንነት ፤ በተለይም የጤና ችግር ከተሰማ ላለመጓዝ መወሰንን  ፤ በአሽከርካሪው እና ተሳፋሪዎች መካከል ያለውን አካላዊ ርቀት መጠበቅን ፤ የእጅ መጨባበጥን ማስወገድን ያጠቃልላል፡፡የህዝብ መጓጓዣ ተጠቃሚዎች የፊት መሸፈኛዎችን ማድረግ የማይጠበቅባቸው ሲሆን ነገር ግን በግል ፈቃዳቸው ተነሳስው ማድረግ ከፈለጉ የሚከለክል ህግ የለም፡፡

https://www.infrastructure.gov.au/transport/files/COVID19_public_transport_principles_29052020.pdf  

የአለማቀፍ ተጓዦች

 እስከ ኦክቶበር 24 2020 ደረስ የሚጓዙ የአለማቀፍ ተጓዦችን በተመለከተ የተቀመጡ ገደቦች የሚከተሉት ናቸው ፦

 • ሜልበርን፤ የአለማቀፍ በረራዎችን ተጠቅመው የሚመጡ ምንም አይነት መንገደኞችን አታስተናግድም
 • ሲድኒ ፤ በቀን 350 መንገደኞችን ብቻ ለማስተናገድ ወሰን አበጅታለች
 • ፐርዝ ፤ በሳምንት 525 መንገደኞችን ብቻ ለማስተናገድ ወሰን አስቀምጣላች
 • ብሪዝበን ፤ በሳምንት 500 መንገደኞችን ብቻ ለማስተናገድ ወሰን አበጅታለች
 • ካንብራና ዳርዊን ፤ የተጓዦች ብዛት በየጊዜው በሚወጡ መመሪያዎች አይነት በአይነት የሚታይ ይሆናል 
 • ሆባርት ፤ ምንም አይነት አለማቀፍ በረራ አይደርገም ፡፡

የተሻሻለ መረጃ ፦

 • ኒው ሳውዝ ዌልስ በሳምንት ተጨማሪ 500 ተሳፋሪዎችን ከ ሴፕቴምበር 27 ፡ 2020 ይጨምራል
 • ኩዊንስላንድ እና ዌስት አውስትራሊያ ተጨማሪ 200 ተሳፋሪዎችን ከ ሴፕቴምበር 27 ፡ 2020 ይጨምራል
 • ኩዊንስላንድ (በ ኦክቶበር 4 )  ዌስተርን አውስትራሊያ (በ ኦክቶበር 11 ) ተጨማሪ 300 ተሳፋሪዎችን በማከል ቁጥሩን ወደ 500 ከፍ ማድረግ ይቻላል፡፡

የየትኛውንም አገር ዜግነት የያዙ በአለም አቀፍ በረራ ወደ አውስትራሊያ የሚገቡ ተጓዦች በሙሉ ወደ ቤታቸው ከመመለሳቸው በፊት በተዘጋጀላቸው ለይቶ ማቆያ ስፍራ ለ14 የመቆየት ግዴታ አለባቸው፡፡

በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደገቡና ከመውጣታቸው በፊት የኮሮና ምርመራ ይደረግላቸዎል፡፡

በለይቶ ማቆያ ስፍራ ውስጥ ለሚኖረው ወጩ የበኩልዎትን እንዲያበረክቱ  ይጠየቁ ይሆናል ፡፡ይህ ሂደት የሚከናወነው በከተሞች እና ክልሎች መንግስት አማካኝነት ነው ፡፡

NSW: https://www.nsw.gov.au/covid-19/travel-and-transport-advice 

VIC: https://www.dhhs.vic.gov.au/information-overseas-travellers-coronavirus-disease-covid-19 

ACT: https://www.covid19.act.gov.au/community/travelling-and-transport 

NT: https://coronavirus.nt.gov.au/stay-safe/quarantine 

QLD: https://www.qld.gov.au/health/conditions/health-alerts/coronavirus-covid-19/protect-yourself-others/quarantine 

SA: https://www.covid-19.sa.gov.au/restrictions-and-responsibilities/travel-restrictions 

TASMANIA:https://www.coronavirus.tas.gov.au/travellers-and-visitors 

WA: https://www.wa.gov.au/organisation/department-of-the-premier-and-cabinet/covid-19-coronavirus-travel-wa 

የአውስትራሊያ ዜጎች እና ቋሚ መኖሪያ ያላቸው በኮቪድ -19 ክልከላ ምክንያት ከአገር መውጣት አይችሉም፡፡

ይሁንና ከአውስትራሊያ ለመውጣት ከፈለጉ በኦን ላይን በማመልከት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለመሆንዎን ማረጋገጥ ይችላሉ፦

 • ጉዞዎ ከኮቪድ 19 ወረርሽን ጋር የተያያዘ እና የእርዳታን ስራ ለማድረግ ከሆነ

 • ጉዞዎ አስፈላጊ የሚባሉ የኢንዱስትሪ እና ንግድ ስራዎችን ( አስመጪ እና ላኪ )  ለማከናውን ከሆነ

 • የሚጓዙት በአውስትራሊያ የማይገኝን የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ከሆነ

 •  የሚጓዙት አስቸኳይ እና ሊቀር የማይችል የግል ጉዳይ ከገጠመዎ

 • ሊከለከል የማይቻልና ለግብረ ሰናይ ስራዎች

 • ጉዞዎ ለብሄራዊ የአገር ጥቅም ከሆነ

የመሸጋገሪያ ቀጠናዎች

የጉዞ መመሪያዎች በአጭር ጊዜ ማሳሰቢያ የሚለወጡ ስለሆነ ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ ከፈለጉ፦

 •  የጉዞ መስመርዎን በተደጋጋሚ መመልከት፤ ከአየር መንገዱ እና የጉዞ ወኪልዎ ጋር መገናኘት ይኖርብዎታል፡፡
 •  በመሸጋገሪያ አየር ማረፊዎች እና በመንግስት ባለስልጣናት የሚነገሩ ማሳሰቢያዎችን ይከታተሉ፡፡
 • ጥያቄዎች ካሉም በአቅራቢያዎ ያሉትን ኢምባሲዎችን እና ቆንስላ ዕ/ቤቶች ያቅርቡ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ድረ ገዕ ይመልከቱ www.smartraveller.gov.au   

የአውስትራሊያ ባለስልጣናት ወረርሽኙን እንዴት እየተቆጣጠሩት ነው ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ መመሪያን ለ Noval Coronavirus ( COVID-19 ) ይፋ አድርገዋል ፡፡

ከኦክቶበር 2020 እስከ ማርች 2021 የ2ቢሊዮን ገንዘብ ለቴሌ ሄልዝ የተመደበ ሲሆን ፤  አገልግሎቱም ለአብላጫው አውስትራሊያውያን በተለይ በአእምሮ ጤና ዙሪያ እንዲዳረስ ለስድስት ወራት እንዲራዘም ተደርጓል ፡፡

ምቹ የሆኑ የክፍያ አይነቶችንም ለነዋሪዎች እና አንስተኛ የንግድ ተቋማትየገንዘብ እጥረት ባጋጠማቸው ወቅት እንዲከፈላቸው ባለስልጣናቱ አድርገዋል ፡፡በዚሀም መሰረት ፦ 

 •  አቅርቦቶች እንድይቋረጡ / የገንዘብ ችግር ያጋጠማቸው አገልግሎቶች
 • ያልተከፈሉ እዳዎች ጊዜ እንዲራዘም እና ያልከፈሉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ስማቸው እንዳይገባ ማድረግ
 • ዘግይቶ በሚከፈሉ ክፍያዎች ላይ የተጣሉ ቅጣቶችን  ፤ ወለዶችን እና እዳዎችን ማንሳት 
 • በእቅድ የሚደረጉ የአገልግሎት መቋረጦችን መቀነስ 
 • ክፍያዎቻቸውን መፈጸም የሚችሉ ባሉበት እንዲቀጥሉ ፤ ይህንንም በማድረግ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ ማደረግ ይቻላል ፡፡

ለተወሰኑ ቪዛ ተጠቃሚዎች የማሻሻያ ለውጦች

የሥራና ሽርሽር ቪዛ ተጠቃሚዎች፤ ለአንድ አሠሪ ለስድስት ወራት የመሥራት ገደብ ተነስቷል፤ እንደ ጤና፣ የአረጋውያን መጦሪያ፣ የግብረ አካል ጉዳተኛ ክብካቤ፣ ሙዋዕለ ሕጻናት፣ ግብርናና የምግብ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠሩ ከሆነና የቪዛ መጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያከትም ስድስት ወራት የቀረው ከሆነ ቪዛ የማራዘም መሥፈርቶችን ያሟላሉ።

የወቅት ሠራተኛ ፕሮግራምና የፓሲፊክ ሠራተኛ ዕቅድ ተሳታፊዎች፤ ቪዛቸውን እስከ አንድ ዓመት ሊያራዝሙ ይችላሉ።

ጊዜያዊ የባለሙያ ቪዛ ባላቤቶች ስራቸውን ከለቀቁ ሌላ አሰሪ እስኪያገኙ ድረስ 60 ቀን መቆየት ያለበለዚያም ከአገር መልቀቅ ይኖርባቸዋል;፡( ያጠራቀሙት ገንዘብም ሆነ ቤተሰብ ቢሮራቸው ) 

ከሥራቸው ተገልለው ግና ሳይቀነሱ ያሉ ከሆነ፤ ወይም የሥራ ሰዓታቸው የተቀነሰባቸው ከሆነ የቪዛ ግዴታቸውን እንደጣሱ አይቆጠረም። በዚህ የፋይናንስ ዓመትም ከጡረታ ተቀማጫቸው እስክ $10,000 ማውጣት ይችላሉ።

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች፤

አለማቀፍ ተማሪዎች ስራ እስካላቸው ደረስ  በአገሪቱ ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ስራ ከሌላቸው ፤ የቤተሰብ ድጋፍ ወይም በቂ ተቀማጭ ገንዘብ ከሌላቸው ሌላ አማራጭ ዘዴዎችን ማሰብ ይኖርባቸዋል፡፡

በአረጋውያን መጦሪያ መስክ የሚሠሩና ነርስ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በሳምንት ከ20 ሰዓታት በላይ መሥራት ይችላሉ።  

 አውስትራሊያ ውስጥ ቢያንስ ለ12 ወራት ያህል የነበሩ ከሆነ ከጡረታ ተቀማጫቸው ማውጣት ይችላሉ። 

፟በቪክቶሪያ የአለማቀፍ ተማሪዎች ለአንድ ጊዜ እስከ $1100 የሚጠጋ ክፍያን የሚፈጸምላቸው ሲሆን ይህም የቪክቶሪያ መንግስት የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ አካል ነው፡፡ በግዛቱም በአሰር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ይጠቅማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጎብኚዎች ፤ ወደ አገራቸው መመለስ ይኖርባቸዋል፤ በተለይም አንዳችም የቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ከሆነ።

 የአዕምሮ ጤናን በተመለከት የሚደረግ ድጋፍ

 • በሁለተኛው ዙር የኮቪድ19 ወረርሽኝ  ሳቢያ ገደብ ውስጥ ለሚኖሩ ነዋሪዎች በሜዲኬር የሚሸፈን ተጨማሪ 10 የሳይኮሎጂ ህክምናን ተገልጋዮች እንዲያገኙ መንገስት  አደርጓል፡፡  
 • የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሰዎች የአእምሮ ጤና ክብካቤ መመሪያ እቅድ  (https://www.healthdirect.gov.au/mental-health-care-plan) የሚያሰፈልጋቸው ሲሆን ፤  ይህንንም የቤተሰብ ሀኪማቸው በየጊዜው የሚገመግም እንዲሁም ተጨማሪ የአእምሮ ጤና ክብካቤን ከሳይኮሎጂስት ፤ ሳይካትሪስት ወይም የጤና ባለሙያዎች የሚያስፈልጋቸው መሆን አለመሆኑን የሚወስን ይሆናል፡፡
 • የመንግስት የአእምሮ ጤና ፖርታል  ( www.headtohealth.gov.au), ከመንግስት የሚገኝ ብቸኛው መረጃ እና መመሪያ ሲሆን በተለይ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና ተለይቶ መቀመጥ በሚያስፈልግበት ወቅት ልጆችን   ፤ በዙሪያችን ያሉትን እና የምንወዳቸም ሰዎች እንዴት እንደምንረዳቸው እና ተጨማሪ የአእምሮ ጤና አገልግሎትንና እንክብካቤን ከየት ማግኘት እንደሚቻል አቅጣጫን ያመላክታል ፡፡  
 • የአውስትራሊያ መንግሥት ኮቪድ-19 ን ለመከለከል እንደምን እየጣረ መሆኑን ለመረዳት Government response  ይጎብኙ።
 • ለተጨማሪ የእንግሊዝኛ መረጃ health.gov.au/news/health-alerts/novel-coronavirus-2019-ncov-health-alert ይጎብኙ። 
 •  የአገር ውስጥ ጉዳዮች - information for the Australian community in your language 
 • የጉንፋን ምልክቶችን ካሳዩ  በቤትዎ ይቆዩ ከዚያም ለሃኪምዎ ወይም የኮሮና ቫይረስ የጤና መረጃ ልዪ መስመር 1800 020 080 በመደወል ምርመራ እንዲደረግልዎ ሁኔታዎችን ያመቻቹ፡፡
 • ዜናዎችን እና መረጃዎች በ 63 ቋንቋዎች ከ sbs.com.au/coronavirus ያገኛሉ፡፡