Coming Up Fri 10:00 PM  AEST
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio

የኮቪድ-19 መረጃ ፦ ቪክቶርያ የተጣለውን ገደብ አራዘመች በኒው ሳውዝ ዌልስ ተጨማሪ 98 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ሆኑ

A person is seen crossing a quiet Flinders Street in Melbourne, Monday, July 19, 2021. Source: AAP Image/Daniel Pockett

ይህ በአውስትራሊያ ጁላይ 19.2021 የተሻሽለ የእርስዎ የኮሮናቫይርስ መረጃ ነው ።

 • የቪክቶርያ የአምስት ቀናት የክልከላ ገደብ ተራዘመ
 • ኒው ሳውዝ ዌልስ ተጨማሪ 98 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎችን ቁጥር አስመዘገበች
 • Service NSW ከአንስተኛ እስከ መካከለኛ ለሚባሉ አገልግሎት ሰጪዎች የኮቪድ-19 ድጎማን እንዲያገኙ ማመልከት እንደሚችሉ ገለጸ
 • አንድ ሚሊየን የፋይዘር ክትባት አውስትራሊያ ገባ ይህም የኮቪድ ክትባትን ስርጭት ከፍ እንደሚያደርገው ተነግሯል ፡፡

ቪክቶርያ

በቪክቶርያ የተጣለው ገደብ ከማክሰኞ እኩለ ለሊት በኋላ እንደማይነሳ ፕሪምየር ዳንኤል አንድሪውስ አስታወቁ ፡፡

ቪክቶርያ ተጨማሪ 13 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከሌላ አገር በመጣ  ሰው አማካኝነት ነው ፡፡

በአሁን ሰአትም 15,800 ቀጥተኛ ንክኪ ያላቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ስፍራ ይገኛሉ፡፡250 የሚሆኑ ለቫይረሱ የተጋለጡ አካባቢዎች ተለየተው የታወቁ ሲሆን ለተጨማሪ መረጃዎች የሚከተለውን ይመልከቱ ፦ locations of the cases in a list or a map.

ኒው ሳውዝ ዌልስ

ኒው ሳውዝ ዌልስ ተጨማሪ 98 የኖሮናቫይረስ ተጠቂዎችን ቁጥር አስመዝግባላች፡፡ ከነዚህ ውስጥ ሁለት ሶስተኛው የሚገኛው በደቡብ ምእራብ ሲድኒ ነው ፡፡ ከተመዘገቡት ውስጥም 61 ያህሉ መነሻቸው የታወቀ ሲሆን የተቀሩት 37ቱ ምንጭን ለማግኛት በምርመራ ላይ ነው፡፡ አዲስ ከተመዘገቡት 20 ያህሉ አስተላላፊ ሆነው በማህበረሳቡ ውስጥ ከአንድ ቀን በላይ ቆይተዋል ፡፡

ለተጨማሪ መረጃዎች የሚከተለውን ይመልከቱ፦ locations of the cases in a list or a map.

በግሬተር ሲድኒ በቅርቡ የተቀመጠው ገደብ እና ክልከላ የግንባታ ሰራተኞችን እና መሰረታዊ ያልሆኑ ተብለው የሚታወቁ የችርቻሮ ነጋዴዎችን የሚያጠቃልል ሲሆን በአንጻሩም መድሃኒት ቤቶች ፤ባንኮች እና የመጠጥ መሸጫ ስፍራዎች ክፍት ይሆናሉ፡፡

Service NSW  ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ለሚባሉ የንግድ ተቋማት በኮቪድ19 ምክንያት ዝግ ለሚሆን ተቋማት ድጎማን እንዲያገኙ ማመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል ፡፡ አነስተኛ የንግድ ተቋማት ከዚህ ቀደም በ2020 የኮቪድ-19 ድጎማን ያገኙ አሁንም ማመልከት ይችላሉ፡፡

ማመልከቻው እስከ ሴፕቴምበር 13, 2021 ከምሽቱ 11፡59 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል ፡፡

ባለፉት 24 ሰአታት በመላው አውስትራሊያ

 • በኩዊንስላድ በማህበረሰቡ ውስጥ ምንም የተላለፈ ቫይረስ የለም
 • ካርጎ የጫነ መርከብ የኮቪድ 19 ምልክቶችን ካሳዪ  በፍሪማንትን ደርሷል  
 • ከ80,000 በላይ የፋይዘር ክትባት ሲድኒ የደረሰ ሲሆን 100,000 የሚሆን ሜልበር ደርሷል

የኢድ አላድሀ በአል ( የመስእዋትነት በአል) ሰኞ ጁላይ 19 የሚጀምር ሲሆን በበአሉ የጸሎት ስነ ስራት ወቅትም ራስን እና ሊሎችን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎችን መውሰድ ይገባል ፦

 • ጸሎትን ከቤት ማድረግን ይምረጡ
 • በርካታ ሰዎች ከሚገኙበት ስፍራ ከመሄድ ይታቀቡ
 • የፊት መሸፈኛ ጭንብልን ያድርጉ
 • የርስዎን የመስገጃ ምንጣፍ ይጠቀሙ

የኮቪድ-19 አፈታርኮች

ጤነኛ ወጣቶች በኮቪድ-19 አይያዙም ፡ የሚገድለውም  አዘውንቶችን እና የጤና ቸግር ያለባቸውን ብቻ ነው ።

የኮቪድ-19 እውነታ

የእድሜ ባለጸጋዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል እንዲሁም ተያያዝ የጤና ችግር ያለባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል ፤ ነገር ግን ጤነኛ ወጣቶችንም ይጎዳል እንዲሁም ይገድላል ።

ለይቶ ማቆያ ፤ ጉዞ፣ የመመርመሪያ ክሊኒኮች ፤ እና የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያ

የለይቶ ማቆያ እና የመመርመሪያ ክሊኒኮች የሚመሩት እና ተግባራቸውን የሚከውኑት  በክልሎቹ እና ግዛቶቹ መንግስታት ነው ፦

NSW Travel & transport and Quarantine
VIC Travel permitOverseas travellers and Quarantine
ACT Transport and Quarantine
NT Travel and Quarantine
QLD Travel and Quarantine
SA Travel and Quarantine
TAS Travel and Quarantine
WA Travel and Quarantine

ወደሌላ አገር መጓዝ ከፈለጉም እና ፈቃድን ለማግኛት ፤ በኦንላይን ፈቃድን  ይችላሉ Click here     

ከአውስትራሊያ ውጪ እንዴት ማጓዝ እንደሚችሉ ተጨማሪ ማረጃን ማግኘት ይችላሉ ። ኣለማቀፍ በረራዎችን በተመለከተ ጊዜያዊ የሆኑ እርምጃዎች በየጊዜው በመንገስት የሚከለሱ እና የሚሻሻሉ ናቸው ስለሆነም ድረገጽን  Smart Traveller ይመለከቱ ።

ዜናዎችን እና መረጃዎችን ከ 60 በላይ ቋንቋዎች ከ sbs.com.au/coronavirus ያግኙ

በሚኖሩበት ክልል እና ግዛት ያለውን ጠቃሚ መረጃ ከ  NSW, VictoriaQueenslandWestern AustraliaSouth AustraliaNorthern TerritoryACTTasmania.  ያግኙ

የኮቪድ-19 ከትባትን በተመለከተ በቋንቋዎ መረጃን ከ  COVID-19 vaccine in your language.  ያግኙ

የኒውሳውዝዊልስ የመድብለ ባህል ጤና ክህለ ተግባቦት አገልግሎት ትርጉም መረጃዎችን  በተመለከተ ፦

COVID-19 Vaccination Glossary
Appointment Reminder Tool.

የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የመመርመሪያ ክሊኒኮችን በተመለከተ ፦

NSW 
Victoria 
Queensland 
South Australia 
ACT 
Western Australia 
Tasmania
Northern Territory 

የእያንዳንዱ ክልል እና ግዛት የወረርሽኝ ጊዜ ክፍያን መረጃ በተመለከተ፦

NSW 
Victoria 
Queensland 
South Australia 
ACT 
Western Australia 
Tasmania
Northern Territory

 

 

  

 

 

 

 

This story is also available in other languages.