Coming Up Fri 10:00 PM  AEST
Coming Up Live in 
Live
Amharic radio

ክትባት ኦሚክሮንን ሊገታ ይችላል? መረጃ ስለ ታካይ ኮቪድ-19 ክትባት

The vaccine technology underlying the booster shots is the same as the first and second vaccine doses. Source: AAP

ክትባት ኦሚክሮንን ሊገታ ይችላል? በርካታ ጠበብት አሁን ያሉት ክትባቶችና ታካይ ክትባቶች አዲሱን ኦሚክሮን ቫይረስ የመከላከል አቅም ሊኖራቸው ይችል ይሆናል በማለት ያመላክታሉ።

አዲሱ ኮቪድ-19 ኦሚክሮን በዓለም የጤና ድርጅት በአሳሳቢ ቫይረስነት ተፈርጇል፤ አሁን ያሉት የኮቪድ-19 ክትባቶች ሊቋቋሙት አይችሉ ይሆናል ከሚል በስፋት የተሰራጨ ይሆናል አባባል ጋር ተያይዞ። 

ምናልባትም ክትባቶቹ አዲስ ቀመሮች ያሿቸው ይሆናል፤ ፋይዘር አሁን ያለውን ክትባት በ100 ቀናት ውስጥ ማሻሻል እንደሚችል ሲገልጥ ሞደርና ተመሳሳይ ውጤት በ2022 መጀመሪያ ላይ ለስኬት ሊያበቃ እንደሚችል አስታውቋል። 

ታካይ ክትባቶችን መከተብ የሚችለው ማን ነው?

የአውስትራሊያ ታካይ ኮቪድ-19 ክትባት ፕሮግራም የተጀመረው ኦክቶበር ውስጥ ሲሆን ከኖቬምበር 8 አንስቶ ታካይ ክትባቶች ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑና የኮቪድ-19 ሁለቱንም ክትባቶች ከተከተቡ ስድስት ወራት ለሞላቸው ሁሉ ስንዱ ነው። 

የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 17 ላሉ ታካይ ክትባቶችን እንዲከተቡ ምክረ ሃሳቡን አልሰጠም፤ የበሽታ መከላከል አቅማቸው በብርቱ ደካማ የሆነ ሰዎች ሁለቱን ዋነኛ ክትባቶቻቸውን ከተከተቡ በኋላ ቀደም ብለው እንዲከተቡ ግና አማክሯል።       

People at the Boondall mass vaccination hub in Brisbane on 18 September 2021.
People at the Boondall mass vaccination hub in Brisbane on 18 September 2021.
AAP

ታካይ ክትባትን በምን ያህል ጊዜ ሊያገኙ ይገባዎታል?

በሽታን የመከላከል አቅማቸው በእጅጉ ደካማ የሆነ ሰዎች ሁለተኛ ክትባታቸውን ከተከተቡ በኋላ ከሁለት እስከ ስድስት ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ሶስተኛ ክትባታቸውን እንዲከተቡ ይመከራል።

በተለየ ሁኔታ፣ ወረርሽኝ በተስፋፋበት ወቅት ወይም በሽታን የመከላከል አቅማቸው በእጅጉ ብሶ ከተዳከመ ምናልባትም ወደ አራት ሳምንታት ዝቅ ሊል ይችላል።

ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉ ሁለተኛ ክትባታቸውን ከተከተቡ በኋላ እስከ ስድስት ወራት መቆየት ይችላሉ።

ታካይ ክትባቶች የሚሠሩት እንደምን ነው?

የክትባት ቴክኖሎጂ ታካይ ክትባቶችን ከመጀመሪያውና ሁለተኛ ጋር በእኩል ይፈርጃቸዋል።

ታካይ ክትባት የተተለመው በሽታን የመከላከል አቅምና ቀደም ያሉት ክትባቶች በሽታን የመቋቋም አቅም በጊዜ ሂደት ዝቅ የማለት ደረጃን በተወሰነ ደረጃ ጠብቆ ለማቆየት እንዲያስችል ነው። 

በሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የኢሙዩኖሎጂና ፓቶሎጂ ዲፓርትመንትዋ ዶ/ር ኢሚሊ ኢድዋርድስ ለታካይ ክትባቶች መጠነ ሰፊ ዕውቀቶች የተካበቱት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የክትባት ፕሮግራሞች አካል የሆኑትን ሄፓታይተስ እና የሰብዓዊ ፓፒሎማቫይረስን ከአካተተ የቀድሞ ክትባቶች እንደሆነ ሲናገሩ፤

ኦክቶበር ላይ ለ SBS "ዋናው ነገር መሠረታዊ ነገሮችን በስፋት አዛንቆ ማዋደዱ ላይ ነው" ሲሉ ገልጠው ነበር። "ቴክኖሎጂው ምናልባትም ለዓመታት እዚያው የነበረ ሊሆን ይችላል፤ ክትባቶችንና ኢሙዩኖሎጂያዊ ቁሶችን አስመልክቶ የምንከታተለው የእርስዎን የክትባትና ቫይረስ ግብረ ምላሽ ነው" ብለዋል። 

የትኛውን ታካይ ክትባት ሊከተቡ ይገባል?

የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ግለሰቡ የትኛውንም ዓይነት ዋነኛ ቀዳሚ ክትባት ቢከተብም፤ ሶስተኛ ክትባቱ ግና የmRNA ክትባት የሆነው ፋይዘርን እንዲከተብ ምክረ ሃሳቡን ሰጥቷል።

መንግሥት ሞደርናን ጨምሮ ሌሎችም ክትባቶች እንዲታከሉ በፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር በኩል ይሁንታ እንደሚቸራቸው ይጠብቃል።

ተመራጭ ባይሆንም እንኳ፤ አስትራዜኒካ ቀደም ብለው ለተከተቡትና አናፊላክሲስ የመሰለ አሉታዊ ክስተት ላልገጠማቸው ሰዎች በሶስተኛ ክትባትነት ሊሰጥ ይችላል። እንዲሁም ቀደም ብለው mRNA ክትባት ሲከተቡ ብርቱ አሉታዊ ክስተት ለገጠማቸው ሰዎችም ሊሰጥ ይችላል። 

እንደምን ቀነ ቀጠሮ ማስያዝ እችላሁ? 

መመዘኛውን ለሚያሟሟሉ ሰዎች በሕክምና ባለሙያ በኩል ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።

በመንግስት Vaccine Clinic Finder ድረገጽ በኩል ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። 

   

A healthcare worker speaks to a patient after administering a Covid19 vaccination at a pop-up vaccination van in Epping, Melbourne.
A healthcare worker speaks to a patient after administering a Covid19 vaccination at a pop-up vaccination van in Epping, Melbourne.
AAP


ታካይ ክትባቶች ምን ያህል ፍቱን ናቸው?

ሳይንቲስቶች አሁን ያሉት ክትባቶች ኦሚክሮንን መከላከል ይችሉ አይችሉ እንደሁ ለማወቅ ጥድፊያ ላይ ናቸው። 

ዴልታን አስመልክቶ ክትባቶቹ ለሆስፒታል ከሚዳርግ ብርቱ ሕመምና ሞትን በተመለክተ በከፍተኛ ደረጃ መከላከል ላይ ይገኛሉ።

ዶ/ር ኢድዋርድ የአውስትራሊያ ባለስልጣናት ገደቦችን እንስተው ክፍት ቢያደርጉም፤ ሌሎች የፊት ጭምብሎችና አካላዊ ርቀቶችን የመሳሰሉ የጤና ቁሶች አሁንም አስፈላጊ ናቸው። ይሁንና ታካይ ክትባቶችን ጨምሮ የክትባቶች አስፈላጊነት ከፍተኛ ዘለቄታ እንዳለው ሲያመላክቱ፤

"ከትባት የተከተቡ ከሆነ፤ ክትባት ካልተከተቡት የበለጠ የመክላከል ዕድል አለዎት። አለመታደል ሆኖም በተወሰነ መልኩ መጋለጥ ይኖራል። ይሁንና ከብርቱ ሕመም ይከላክልልዎታል protect you against severe disease ይህ በተለይም በሉላዊ ወረርሽኝ ወቅት በጣሙን ጠቃሚ ነው" ብለዋል። 

ሌሎች ተጋላጭነት ወይም የጎንዮሽ ጉዳቶችስ ይኖራሉ?

ታካይ ክትባቶች እንደ መጀመሪያዎቹ ሁሉ ተመሳሳይ ናቸው። የጎንዮሽ ጉዳቶችን አስመልክቶ ያለው ምክር ቀደም ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት ነው። ሆኖም በመላው ዓለም የጤና ባለስልጣናት ሌላ ዘላቂ ጉዳቶች ይኖሩት እንደሁ ለማወቅ በቅርበት እየተከታተሉ ናቸው።  

ለሁሉም የሚበቃ የክትባት መጠን አለን?

ኦክቶበር ውስጥ ግሬግ ሃንት አውስትራሊያ ታካይ ክትባቶችን ለማዳረስ በብቁ ስንዱ መሆኗን ሲገልጡ፤  

"ከ151 ሚሊየን በላይ ፋይዘር፣ ኖቫቫክስና ሞደርና ከወዲሁ የአቅርቦት ዋስትናቸው ተረጋግጧል፤ የሕክምና ጠበበት ይሁንታዎች እንደተገኙ አውስትራሊያ ታካይ ክትባቶችን ለማቅረብ በብቃት ተሰናድታለች" ብለዋል። 

የተላላፊ በሽታዎች ተጠባቢ ሳንጄይ ሰናናያኬ ቀደም ብለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ታካይ ክትባትን አስመልክቶ የተካሄደው ውይይት የመጀመሪያና ሁለተኛ ዙር ክትባቶችን ያዳረሱ የበለፀጉ አገራትን የክትባት ፍትሃዊ ክፍፍልን አስመልክቶ በአደባባይ እንዳጋለጣቸው ሲናገሩ፤

"በመጨረሻም፤ አውስትራሊያ ውስጥ ለብርቱ ሕመሞች ከመጋለጥና ለሆስፒታል ከመዳረግ ራሳችንን የተከላከልን ቢሆንም፤ የተቀረውን ዓለምም ለመታደግ መጣር አለብን" ያሉ ሲሆን፤ አክለውም "የኮቪድ-19 ክትባትን አስመልክቶ ከራስ ወዳድነት ለመራቅ ራስ ወዳድ መሆንን አለብን" ብለዋል የእስያ ፓስፊክ ሪጂን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ማድረግን ለማመላከት። 

[may]

[in Australia]

This story is also available in other languages.