Advertisement
1497items
የመጀመሪያው አገር በቀል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ኋላም የኤርትራ ሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ሊቀመንበር የነበሩት ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ፤ በክፍል አምስት ቃለ ምልልሳችን የሕይወት ጉዞ ታሪካቸውን ያጠቃልላሉ።መንደርደሪያቸው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በባድመ ጦርነት መቀስቀስ ሳቢያ ‘ጦርነቱ ያለ ፓርላማና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሁንታ እንደምን ታወጀ?’ ብለው የተቃውሞ...
የክፍል አራት የፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ ግለ ሕይወት ትረካ መነሻ በቀድሞው የኢሕዲሪ መንግሥትና በአማጽያን ኃይላት መካከል ተካሂደው ለስኬት ያልበቁን የአትላንታ፣ ኬንያና ሎንዶን የሰላም ድርድር ጥረቶች ናቸው።ነገን አማትረው በማየትም፤ የአሰብ ጉዳይ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ያሉ ችግሮች ሲፈቱ በድርድር አብሮ ተፈቺ ሊሆን እንደሚችል ያስባሉ።
ፕሮፌሰር በረከት በትናንቱ የኤርትራ ሕዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት መሪና ዛሬም ድረስ ለ፳፮ ዓመታት ኤርትራን በፕሬዚደንት እየመሩ ያሉትን ኢሳይያስ አፈወርቂን ማንነት በውል ለመረዳት እንደምን እንዳዳገታቸው ያነሳሉ።
አገርኛ ሪፖርት፤ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ከቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ  ወደ ኬንያ የሸሹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 8592 እንደደረሰ የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር ማስታወቁን ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል።የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎቹ የኬንያን ድንበር ተሻግረው ለመጠለል ግድ የተሰኙት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥራ አስፈጻሚ ዕዝ መምሪያን ግዳጅ ለመወጣት በተሰማራ አንድ የሻለቃ ጦር አባላት የተፈጸሙት...
የአውስትራሊያ ፌዴራል ዘውጌ ማኅበረሰባት ምክር ቤት፤ ባሕር ማዶ የተወለዱ መጤዎች ዘንድ ተከስቶ ያለው የቤት አልባነት ቁጥር መናር በጣሙን አሳስቦኛል እያለ ነው።በ2016 ይፋ በሆነው የአውስትራሊያ ስታቲስቲክስ ቢሮ አኃዝ መሠረት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ አውስትራሊያን ከረገጡ መጤዎች ውስጥ 15 ፐርሰንት ያህሉ መጠለያ አልባዎች ናቸው።
አቶ ታዘበው አሰፋ፤ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዲኃን) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳዮችና የድርጅታቸውን ልዑካን ቡድን የአሥመራ ቆይታ አንስተው ይናገራሉ።
በክፍል ሶስት የፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ ግለ ሕይወት ትረካ የሚያጠነጥነው፤ እንደምን የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ከአቋቋመው የመርማሪ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበርነት መንበራቸው ተነስተው የኤርትራ አማፂያንን ለመቀላቀል እንደበቁ ነው።
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የግምገማና አቅጣጫ ቅየሳ ስብሰባ  ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል።
አቶ ጀማል ድሬ ከህሊፍ፤የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፤ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን ከወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው፤ እንዲሁም፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንድምታ አንስተው ይናገራሉ።
የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር በጅሮንድ፤ ማኅበሩ መጋቢት ፱ ማርች 18 ስለ ጠራው አጠቃላይ ስብሰባ አጀንዳ ይናገራሉ።
የበርካታ የንግግር ነፃነት ሽልማቶች ተሸላሚው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ያለውን ፅኑ ዕ አቋምና እምነት ይገልጣል።በእሥር ጊዜያቱ ድጋፋቸውን ለቸሩት ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላትም ምሥጋናውን ያቀርባል። 
ጋዜጠኛ ማርያማዊት ኤልያስ ኮስላይ ጋር እንደምን ወደ ሙያው ተስባ እንደዘለቀችና ስለ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሚና ትናገራለች።
ፕሮፌሰር በረከት ሃብተስላሴ፤ በክፍል ሁለት የግለ ሕይወት ትረካቸው የዓይን ምስክርና ተሳታፊ የነበሩባቸውን ሁለት አንኳር የታሪክ ምዕራፎችን ያነሳሉ።የ1953ቱን የታህሳስ ‘ግርግር’ እና የየካቲት ‘66ቱን የአብዮት ‘ፍንዳታ’ ታሪካዊ ክስተቶች።
በታህሳሱ ግርግር ወቅት በአብዮት ቀስቃሽነትና መሪነት ለክስ የተዳረጉትን በዳኝነት ተሰይመው እንዲፈርዱ በልዑል ዓሥራተ ካሣ ይመረጣሉ። እሳቸው ራሳቸው ከለውጥ ፈላጊዎቹ አንዱ ነበሩና በአለቆቻቸው ፊት ሞገስን ለመላበስ ሲሉ ከታሪክና ከኅሊናቸው ጋር መጋጨትን አልወደዱም። ይልቁንም ምርጫ አድርገው የዘየዱት ከአዲስ አበባ መሰወርን ነበር። “የታሪክ አውራ የሆኑና የማከብራቸው [እነ ጄኔራል መን...
አገርኛ ሪፖርት፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን የኢትዮጵያ ጉብኝት ቀዳሚ ትኩረቱ አድርጓል።
የበርካታ የንግግር ነፃነት ሽልማቶች ተሸላሚው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በሽብር ክስ እንደምን የ፲፰ ዓመታት እሥር ተበይኖበት ዘብጥያ እንደወረደና ከስድስት ዓመታት ተኩል የእሥራት ጊዜያት በኋላ እንደተለቀቀ ይናገራል።ለስምንት ጊዜያት በተደጋጋሚ ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር፤ የእሥር ጊዜያቱ ‘እምነትና ዲሞክራሲ’ ፅኑዕ የሕይወቱ ማዕከል እንዲሆኑ ጉልህ ሚና ማሳደራቸውን ይገልጣል።  
የሥራ መደብ ስልጠና፤ ለወጣት መጤዎች ወደሚሹት የሥራ ዘርፍ ለመዝለቅ አንዱ ማለፊያ መንገድ ነው።የሥራ መደብ ስልጠና የክፍያ ሥራን ከልምምድ ጊዜያት ጋር ያጣመረ ነው። በሙሉ ወይም በግማሽ ቀናት ሰልጣኝነት፤ አሊያም ትምህርት ቤት ሳሉ መከወን ይቻላል።