Come Fly With Us: Esayas Woldemariam Hailu

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰባት አሠርት ዓመታት በላይ ዘመን ያሸመገለች፤ በስመጥር የበረራ ተቋምነቷ ለአገር ቅርስነት የበቃች፤ በመልካም ሬኮርዷ ዓለም አቀፍ ሞገስን የተላበሰች ናት። የኢትዮጵያውያንን ልብ በፍቅር በማማለሏም በአንቺታ “የኢትዮጵያ” በሚል ቁልምጫ ትሞካሻለች።

Esayas

Esayas Woldemariam Hailu, MD Ethiopian International Services Source: SBS Amharic

በሰባ ሁለት ዓመታት በረራዋ ከDouglas DC-3 ጢያራነት እጅጉን ዘመነኛ የሆነው Airbus A350-900 ጨምራ የ100 አውሮፕላኖች ባለቤት በመሆን ከአፍሪካ አቻ የለሽ አየር መንገድ ለመሆን በቅታለች።
Douglas DC-3
ተጠዋሪዋ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጢያራ Source: SBS Amharic
የኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ በቦሌ Source: SBS Amharic
የኢትዮጵያ - በመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ብቻ የተወሰነች ባለመሆኗም ከጥገና እስከ ዕቃ ማጓጓዣ ግልጋሎቶችን ትሰጣለች።
Maintenance
ጥገና Source: SBS Amharic
Cargo
የዕቃ ማጓጓዣ Source: SBS Amharic
ከራሷም አልፋ የባሕር ማዶኛ የበረራና አስተናጋጆችንንና አብራሪዎችን ሳይቀር በአካዳሚዋ አሰልጥና ለአየር ታበቃለች።  

  
Hostess
የበረራ አስተናጋጆች ስልጠና Source: SBS Amharic
አቶ ኢሳያስ ወልደማርያም ኃይሉ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ማኔጂንግ ዳይሬክተርም በአዲስ አበባ ዋና መስሪያ ቤታቸው ስኬትን ትህትና አላብሰው  ያወጉን ይህንኑ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሰባ ሁለት ዓመታት ጉዞ፣ የአገር ምጣኔ ሐብታ ታዳጊነትዋን፣ የፓን አፍሪካኒዝም አስፋፊነቷን፣ ከሰሞነኛው አወዛጋቢው የከፊል ፕራይቬታይዜይሽን ጉዳይ ጋር አዛንቀው።
Esayas
Esayas Woldemariam Hailu MD Ethiopian International Services Source: SBS Amharic
ከትልማቸውን ነቅሰውም አውስትራሊያን አካትቶ የአየር መንገዷ ክንፎች ወዴት ለመቅዘፍ እንደተሰናዱ ፍንጭ ሰጥተዋል።

 

ኢትዮጵያውያን አብዝተው የአየር መንገዱ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑም ጋብዘዋል።


Share
1 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS Amharic

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service