ምንም እንኳ የአካል ጉዳቶችን ያህል አንስተን ባንነጋገርባቸውም፤ የአዕምሮ ጤና ችግሮችም እውን ናቸው። ባለፈው ዓመት ብቻ፤ ከአምስት አንድ አውስትራሊያውያን በተለያየ መልኩ የአዕምሮ እክል ገጥሟቸዋል።
ከሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ
ከአዕምሮ ጤና ጋር እየታገሉ ያሉ ከሆነ ሐኪምዎን ያነጋግሩ።
ዶ/ር ስቴፈን ካርቦን ሐኪም ዘንድ የመቅረቡን ፋይዳ ሲያስረዱ “የጠቅላላ ጤና ሐኪም መጠነኛ ፍንጭ ለማግኘት፣ ምርመራን ለማድረግና ሲልም ወደ ሥነ ልቦና ሐኪም ወይም ወደ ሌላ የአዕምሮ ጤና ተጠባቢ ዘንድ ለመመራት ትልቅ መነሻ ይሆናቸዋል።” በማለት ለ SBS ገልጠዋል።
ሐኪሞችና አስተርጓሚዎች ጉዳይዎን ለማንም ሳይገልጡ አክብረው ይይዛሉ፤ በግል አንስተው የነገሩዋቸውን ጉዳዮች ጠብቀው የመያዝ ሕጋዊ ግዴታ አለባቸው።
እንግሊዝኛ ተናጋሪ ላልሆኑና የትርጉም ግልጋሎቶችን ለሚሹ አማራጭ አገልግሎቶችን በብሔራዊ የትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎቶች ተቋም በኩል ሊያገኙ ይችላሉ።
ክፍያውን እንደምን ሊቋቋሙት ይችላሉ?
የሜዲኬይር ሥርዓት በየዓመቱ እንደምን እስከ 10 ጊዜያት ያህል የሥነ ልቦና ሐኪም ወይም ሌላ የአዕምሮ ተጠባቢን የሕክምና ግልጋሎቶች ለማግኘት መደጎም እንደሚችሉ Better Access initiative ይመራዎታል።
ገቢዎ ዝቅተኛ ከሆነ፤ በዓመት እስከ 12 (አንዳንዴም እስከ 18) ጊዜያት ያህል የሥነ ልቦና ግልጋሎቶች ሕብረትን ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን መመዘኛውን ሊያሟሉ ይችላሉ።
የእነዚህ ግልጋሎቶች ተጠቃሚ ለመሆንና የክፍያ ተመላሽም ለማግኘት ወደ ልዩ ባለሙያ መመራትና የአዕምሮ ጤና ክብካቤ ፕሮግራም ከሐኪምዎ ማግኘት ያሻዎታል።

ምንም እንኳ በሜዲኬይር በኩል እገዛ ባያስገኝልዎትም፤ አውስትራሊያ ውስጥ ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች በርካታ የማኅበረሰብ ማዕከላትና ድርጅቶች የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።
የስልክ ወይም ኦንላይን ድጋፍን ማግኘት
በአካል ተገኝተው ለመነጋጋር ምቾት የማይሰማዎ ከሆነ ወይም አስቸኳይ እገዛ ካስፈለገዎ፤ በስልክ ወይም በኦንላይን ድጋፍ ሊያገኙ ይችላሉ።
Beyondblue የ 24/7 የእርዳታ መስመር አለው፤ በ 1300 22 4636 መደወል ይችላሉ። እንዲሁም chat service ከ 3 PM እስከ 12 AM, 7 ቀናት በሳምንት መጠቀም ይችላሉ። እንዲሁም፤ email them (ኢሜይል በመላክ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ ያገኛሉ)
ለአስቸኳይ እርዳታ Lifeline 24/7 በእርዳታ መስመር በ 13 11 14 እንዲሁም chat service ከ 7 PM እስከ 4 AM። በተጨማሪም Suicide Call Back Service ማግኘት ይችላሉ።
የአስተርጓሚ ግልጋሎቶች
የቋንቋ ድጋፍ የሚያሻዎት ከሆነ፤ ብሔራዊ የትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎቶች ተቋምን በ 131 450 በመደወል ሊያገኙት የሚሹትን ድርጅት እንዲያገናኝዎት ይጠይቁ። እንዲሁም፤ በብሔራዊ የትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎቶች ተቋም በኩል የጠቅላላ ጤና ሐኪምዎንና የሥነ ልቦና ሐኪምዎን ሲጎበኙ አስተርጓሚ በሥፍራው እንዲገኝልዎት ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።
ሰዎችን ያናግሩ

Share

