የራስዎንና የወሲብ ተጓዳኝዎን ጤንነት ለመጠበቅ ሊያውቋቸው የሚገቡ ጥቂት መዘርዝረ ዕውነታዎችን እነሆ፤
ዋነኛ በወሲባዊ ተላላፊ በሽታ መያዣዎች ምንድናቸው?

ወሲባዊ ተላላፊ በሽታዎች chlamydia, syphilis, gonorrhoea, genital warts, genital herpes, thrush እንዲሁም HIV እና hepatitisን ያካትታል። የጤና ድርጅቱ ቀጥታ-ጤና፤ ወሲባዊ ተላላፊ በሽታዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በሚደረጉ አካላዊና አፋዊ ወሲባዊ ተራክቦ እንደሚተላለፉ ይገልጣል።
በወሲባዊ ተላላፊ በሽታ መያዜን እንደምን ላውቅ እችላለሁ?

በርካታ ተላላፊ ወሲባዊ በሽታዎች የግድ ምልክቶችን የሚያሳዩ አይደሉም። ለምሳሌ ያህል አውስትራሊያ ውስጥ ይበልጥ ጎልቶ የተለመደው ወሲባዊ ተላላፊ በሽታ chlamydia ነው፤ በአብዛኛውም የሚያጠቃው ወጣቶችን ሆኖ ሳለ፤ ይሁንና ሶስት አራተኛ ያህሉ በክላሚዲያ የተጠቁ ሰዎች የህመሙ ምልክቶች አይታዩባቸውም። እንዲያም ሆኖ ግና ህመሙ በአንድ አንቲባዮቲክስ ልከ መጠን የሚፈወስ ነው።
ውስጣዊ መረበሽ የሚሰማዎት ቢሆንም እንኳ፤ ወሲባዊ የጤና ምርመራ ለማድረግ ሐኪምዎን አዘውትረው መጎብኘቱ ጠቃሚ ነው። የጤና ባለ ሙያዎች ስለ ሆኑና የህክምና መስጫ ስፍራቸው ላይ ያሉትም የህክምና እርዳታ ሊያደርጉ ነውና እነሱን መጎብኘቱ ምንም ዓይነት ውስጣዊ መረበሽን ሊያሳድርብዎ አይገባም።
ወሲባዊ ተላላፊ በሽታዎች አረጋውያን አውስትራሊያውያንንም ያጠቃሉ

ምንም እንኳ ልጅ የመውለድ ዕድሜ ላይ ያሉ ባይሆኑም ከወሲባዊ ተላላፊ በሽታ የተሰወሩ ይሆናሉ ማለት አይደለም። ቆየት ብሎ ተካሂዶ የነበረ Australian Study of Health and Relationships እንደሚያሳየው፤ ዕድሜያቸው በ60ዎቹ የሚገኙ ሰዎች በየጊዜው ወሲብ ይፈጽማሉ፤እንደ National Notifiable Diseases Surveillance System ጥናታዊ ምልከታም በአለፈው አንድ አሠርት ዓመት ውስጥ በአረጋውያኑ ዘንድ በክላሚዲያ የመጠቃታቸው መጠን በ 190 ፐርሰንት አድጓል። ስለሆነም፤ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሁሉ ወሲባዊ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ጥረቶችን ሊያደርጉ ይገባል።
በወሲባዊ ተላላፊ በሽታ መያዜን እንደምን ላውቅ እችላለሁ?

Health check-ups are important to identify potential risk factors.
ካልተመረመሩ በስተቀር የሚያውቁበት መንገድ አይኖርም። ምናልባትም በወሲባዊ ተላላፊ በሽታ ተይዣለሁ የሚል ጥርጣሬ ውስጥዎ ካለ፤ ሐኪም፣ በአካባቢዎ የሚገኝን የቤተሰብ ምጣኔ ክሊኒክ ወይም የወሲብ ጤና ማዕከልን ሊጎበኙ ይገባዎታል።
ለወሲባዊ ጤና ምርመራ የወሲብ ጤና ማዕከልን ሲጎበኙ ሜዲኬይር ካርድ እንኳ አያስፈልግዎትም።
በወሲባዊ ተላላፊ በሽታ ከመያዝ እንደምን ራሴን ልጠብቅ እችላለሁ?

ወሲብ ሲፈጽሙ ኮንዶም መጠቀም በወሲባዊ ተላላፊ በሽታ ከመያዝ ራስዎን በአብዛናው ሊጠብቁ ይችላሉ። የወሲብ ጤና ባለሙያዎች አካላዊም ሆነ አፋዊ ወሲብ በፈጸሙ ቁጥር ኮንዶሞችን እንዲጠቀሙ ምክረ ማሳሰቢያ ይሰጣሉ።
የቋንቋ አገልግሎቶች
ለ 24 ሰዓታትና 7 ቀናት አስቸኳይ የትርጉም ግልጋሎት 131 450 መደወል ይቻላሉ። አስተርጓሚ የሚያሻዎት ከሆነ የሚጎበኙት ክሊኒክ በቀጠሮ ወቅት የፊት-ለፊት አስተርጓሚ ሊያቀርብልዎት ይችላል።