Watch FIFA World Cup 2026™ LIVE, FREE and EXCLUSIVE

“ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመትን እመኛለሁ” - የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንቶኒ አልባኒዚ

ለሁላችሁም መልካም አዲስ ዓመት።

Opposition Leader Anthony Albanese

Opposition Leader Anthony Albanese Source: AAP

ኢትዮጵያ ውስጥ የዝናቡ ወቅት እያበቃ ነው፤ የአደይ አበባ አበባዎችም እያበቡ ነው።

ጊዜው የለውጥ ነው።

ጊዜው የዕደሳ ነው።

የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲም በዚህ ማለፊያና እውነተኛ መንፈስ ነው የሚዘልቀው።

የእናንተ አዲስ ዓመት በወርኃ ሴፕተምበር ነው፤ ኢትዮጵያም ወደ 2012 ዓመተ ምህረት እየዘለቀች ነው።

የቀን መቁጠሪያችሁ በእውነተኛነት የኢትዮጵያን ዘመን ያሸመገለ ታላቅ ታሪክ የሚያንጸባርቅ ነው።

አያሌ ሌሎች አገራት በታሪክ ማዕበል ሲዋጡና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን አገዛዝ የራሳቸውን የዘመን ቀመር ሲለውጡ፤ እናንት ግና የራሳችሁን የቀን መቁጠሪያ ጠብቃችሁ ቆይታችኋል።

የእናንት የዘመን መቁጠሪያ፤ ልክ እንደባሕላችሁ ሁሉ ጥንታዊነቱን የጠበቀ ነው።

ሁሉም ነገር እንዳለ አይቆምምና የቅርብ ዓመታቱን እንኳ ሳንነቅስ - ኢትዮጵያ በታላቅ ለውጦች ውስጥ አልፋለች።

ይሁንና አዲሱን ዓመት ስታከብሩ፤ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን - ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ፔንቴኮስታልና ሌሎች የክርስቲያን ቡድናትን አክሎ በተስፋና በስምምነት አንድ ለመሆን ማለፊያ ጊዜ ነው።

ጊዜ በማይሽረው ብልኃት የተቀረውን ዓለም ልብ ለማሰኘት፤ በአንድ ላይ ስታብሩ ብርቱና መልካም ትሆናላችሁ።

ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመትን እመኛለሁ።

አመሰግናለሁ።

አንቶኒ አልባኒዚ

የተቃዋሚ ቡድን መሪ


1 min read

Published

Updated

By Anthony Albanese




Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Listen to our podcasts

Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now