Settlement Guide: 10 tips for parents to talk about drugs

አደንዛዥ ዕፅን መጠቀም በተወሰኑ ባህላዊና ቋንቋዊ ዝንቅነት ባላቸው ማኅበርሰባት ውስጥ ብርቱ አሉታዊ ገጽታ ስላለው ስለ አደንዣዥ ዕፅ ማንሳቱ አዋኪ ተግባር ሊሆን ይችላል። ልጆችዎ ከእርስዎ ጋር አደንዛዥ ዕፅን አስመልክተው እንዲወያዩ ለማበረታት 10 መንገዶችን እነሆ።

10 tips for parents to talk about drugs

Drugs Source: Getty Images

፩ በሕይወታቸው ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ይኑርዎ

ፍላጎታቸውን አስመልክቶ እርስዎም የፍላጎታቸው ተጋሪነትዎን ያሳዩዋቸው፤ አንዳንድ ነገሮችን አብሮዋቸው አዘውትረው የመከወን ልማድን ያዳብሩ። በየዕለቱ አብሮ ከመመገብ ጀምሮ ከቤተሰብ ጋር ጊዜን አብሮ ማሳለፍ በጣሙን ጠቃሚ ነው።

Be an active part of their lives
Source: Getty Images

፪ ልጆችዎን ያድምጡ

ችግሮቻቸውን ለእርስዎ ለማካፈል ምቾት እንዲሰማቸው ያድርጉ፤ የእነሱ አተያዮች ዋጋ እንዳላቸው ልብ ለማሰኘት የቤተሰብ ውሳኔዎች ላይ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩ ይጠይቋቸው።

Listen to your kids
Source: Getty Images

፫ አርአያ ይሁኗቸው

የእርስዎ ባህርይ በእነሱ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ዝቅ አድርገው አይመልከቱ፤ በተለይም አልክሆል፣ ወይም ትምባሆ፣ ወይም የተዛባ መድኃኒት አጠቃቀምን በተመለከተ።

Be a role model
Source: Getty Images

፬. እውነተኛ ይሁኑላቸው

ስለ አደንዛዥ ዕፅ ሁሉንም ነገር አለማወቅዎ እንግዳ ነገር አይደለም። እርስዎ እውነተኛና ግልጽ አቋም ካለዎት፤ ልጆችዎም በቀላሉ ለእርስዎ ግልጽ ለመሆን ይቀላቸዋል።

Be honest with your kids
Source: Getty Images

፭. ተገቢ ጊዜን ይጠቀሙ

ከልጆችዎ ጋር ስለ አደንዛዥ ዕፅ ሲነጋገሩ ተገቢ ጊዜን መምረጥዎን ያስተውሉ። ምናልባትም ሁላችሁም ቴሌቪዥን እየተመለከታችሁ፣ ወይም እነሱ ትምህርት ቤታቸው ስላለ ግለሰብ፣ አሊያም ስለ ቡድን ጓደኞቻቸው እያወሩ ሳለ መሆኑን።

Pick your moment
Source: AAP

፮. ረጋ ይበሉ

ስለ አደንዛዥ ዕፅ በሚያነሱበት ወቅት ረጋ ማለትና ሚዛናዊ መሆን በጣሙን ጠቃሚ ነው፤ እንዲሁም ከሚገባው በላይ ነገሮችን አጋንኖ አለማቅረብ። ሲናገሩ ከማጣጣልና በስብከት መልክ ከመግለጽ ይቆጠቡ፤ አሊያ ለወደፊቱ አደንዛዥ ዕፅን አስመልክቶ የሚያደርጉት ውይይቶች ሳንካ ይገጥማቸዋል፤ ልጆችዎንም ከእነ አካቴው ለመነጋገር ፈቃደኞች እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል።

Be calm
Source: Pixabay/Public Domain

7. ግጭትን ያስወግዱ

ግጭት ሰፍኖ ሳለ ችግርን ለመፍታት አዋኪ ይሆናል። ፍጥጫው ከከረረ ንግግርዎን ይግቱና በሁለታችሁም ዘንድ መረጋጋት ሲሰፍን ይመለሱበት።

Avoid conflict
Source: Pixabay/Public Domain

8. መነጋገርዎን ይቀጥሉበት

አንዴ አደንዛዥ ዕፅን በተመለከተ ውይይት ከጀመሩ ቀጥለውም ሌላ ውይይት ማድረጉ ጠቃሚ ነው። ከልጆችዎ ጋር ቀደም ብለው ስለ አደንዛዥ ዕፅ መነጋገር ይጀምሩ፤ በማናቸውም ጊዜም ከልጆችዎ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ ይሁኑ።

Keep talking
Source: Getty Images

9. ግልጽ የሆነ ወሰን ያብጁ

አደንዛዥ ዕፅ ያለበት ሁኔታዎች ሲገጥማቸው ልጆችዎ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይወያዩ፤ ይስማሙ። ለምሳሌ ያህል፤ በማናቸው ሰዓት ቢሆን ካሉበት ድረስ መጥተው እንደሚወስዷቸው ያስታውቋቸው። ሆኖም፣ መጀመሪያውኑም እንዲያ ላለ ሁኔታ ራሳቸውን በፍጹም ሊያጋልጡ እንደማይገባቸው ግልጽ ሊያደርጉላቸው ይገባል።

Set clear boundaries
Source: Getty Images

፲. አዎንታዊነት ላይ ያተኩሩ

ስለ ራሳቸው መልካም ስሜት እንዲሰማቸው ያበረታቱዋቸው፤ ከበሬታ እንድሚገባቸውና ራሳቸውንም ማክበር እንዳለባቸው ያሳውቋቸው።

Image

አደገኛ ዕፅ: የእውነታ መዘርዝርን የያዙ የህትመት ውጤቶችና ለወላጆች የሚሆኑ ምክር ለበስ አተያዮች በ13 ቋንቋዎች ተጽፈው ይገኛሉ።

የአልክሆልና አደንዛዥ ማዕከላት በክልልና ክፍለ ግዛት መንግሥታት በኩል፤ የመረጃ፣ ምክር፣ አግባብ ወዳላቸው ድርጅቶች የመምራት፣ የመቀበል፣ ግምገማ የማድረግና በቀን የ24 ሰዓታት ያልተቁረጠ ድጋፍ ይሰጣሉ። ግልጋሎቶቻቸውንም ለግለሰቦች፣ ለቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው፣ ሐኪሞች፣ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች፣ የንግድና ማኅበረሰባት ቡድናት ይሰጣሉ።


Share

1 min read

Published

Updated

By Ildiko Dauda

Presented by Kassahun Seboqa



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Listen to our podcasts

Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now