፩ ስለ ደሜንሽያ ምልክቶች የግንዛቤ ማነስ
በተወሰኑ ማኅበረሰባት ዘንድ የደሜንሽያ የይሆናል እሳቤዎች ከደዌ፣ የአእምሮ ሕመም፣ እርጅና ጋር ተያይዞ፤ አሊያም ከነአካቴው ትርጉም የለሽ ሆኖ ይታያል። ደሜንሽያ በተለያዩ የአእምሮ ህመሞች ሳቢያ የሚከሰት፤ የማስታወስና የማሰብ ችሎታን፣ የባህሪይ ለውጥን የሚያስከትልና የዕለት-ተዕለት ክንውኖችን የሚያውክ ህመም ነው።

፪ ደሜንሽያን ከተፈጥሯዊ እርጅና ጋር አያይዞ መመልከት
የተወሰነ ማኅበረሰባት ውስጥ ደሜንሽያ የተፈጥሯዊ እርጅና አካል ተደርጎ ይታያል። ምልክቶቹ ምን እንደሆኑ ቀደም ብሎ በውል ባለመገንዘብ፣ እርዳታ ለመጠየቅም ወዴት መሄድ እንደሚገባ ባለማወቅ፤ ወይም ከሃፍረትና ስም ይወጣልኝ ይሆናል ብሎ ከማሰብ የተነሳ ዘግይቶ በመመርመር ለቀውስ ከመዳረግ ላይ ይደርሳሉ።

፫ ደሜንሽያን ከሃፍረት ጋር ማያያዝ
በርካታ ሰዎች "እብድ" ተብለን እንጠራ ይሆናል በሚል ፍራቻ ስለ በሽታው በግልጽ መናገርን አይሹም። በሳቢያውም ከቡድን እንቅስቃሴዎች ተሳትፏቸውን ይቀንሳሉ፤ ከማኅበራዊ ቡድናት ክንዋኔዎችም እንዲሁ ይነጠላሉ።

፬ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዝቅተኛ ክህሎት አስባብ ለተግባቦት ተግዳሮት መዳረግ
በደሜንሽያ ጅማሮ ሳቢያ የተወሰኑ ሰዎች የነበራቸውን የእንግሊዝኛ ክህሎት ያጡና ወደ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይመለሳሉ።

፭ ሰዎች በቤተሰብ አባላት ክብካቤን ያገኛሉ የሚል የተዛባ አተያይ
በተወሰኑ ማኅበርሰባት ውስጥ ቤተሰብ ወይም ልጆች የደሜንሽያ ታማሚ ወላጆቻቸውን ይከባከባሉ የሚል ብርቱ እሳቤ አለ። ይሁንና፤ ባህላዊ ዕሴቶች ከአዲሱ አውስትራሊያዊ ዕሴቶች ጋር ሲዛነቁ የበርካታ አረጋውያን ዕውነታ የተለየ ሆኖ ይገኛል።

በብሔራዊ ደሜንሽያ የእርዳታ መስመር 1800 100 500 በመደወል የምክር አገልግሎት ድጋፍ ያገኛሉ።
አስተርጓሚ የሚሹ ከሆነም የብሔራዊ ደሜንሽያ የእርዳታ መስመርን 131 450 በመደወል የስልክ ትርጉም አገልግሎት ሊያገኙ ይችላሉ።
Share

