፩. ለህሙማን ተከባካቢ የድጋፍ ቡድኖች እገዛ
እንግሊዝኛ ለማይናገሩ የህሙማን ተከባካቢዎች የአገልግሎት እገዛዎችን ለማግኘት በጣሙን አዋኪ ነው። ሆኖም በርካታ ባህልንና ቋንቋን መሠረት ያደረጉ የድጋፍ ቡድኖች በመላው አገሪቱ ይገኛሉ።

፪. የምክር አገልግሎት አገዛ
የባህላዊና ቋንቋ ዝንቅነት ያላቸው የህሙማን ተከባካቢዎች ማኅበራዊ ገለልተኛነት፣ የቋንቋና ባህል ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል፤ አዘውትረውም እርዳታን አይጠይቁም። የህሙማን ተከባካቢዎች በሕይወታቸው ውስጥ ሚዛንን ለማስጠበቅና አስቸጋሪ ሁነተቶችን ለመቋቋም ይቻላቸው ዘንድ ብልሃቶችን ለማፈላለግ የምክር አገልግሎቶች አሉ።

፫. የዕረፍትና ዕለታዊ ፕሮግራሞች
ክብካቤ የሚደረግላቸው ሰዎች ዕለታዊ ፕሮግራሞች ካሏቸው ወይም ሌላ አገልግሎቶችን የሚያገኙ ከሆነ ለህሙማን ተከባካቢዎች ጫናቸውን በመጠኑ ይቀንሳሉ። Carer Support ከእንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ የህሙማን ተከባካቢዎችን የሚያግዝበት የተለያዩ አማራጮች አሉት።

፬. ለህሙማን ተከባካቢዎች ከሴንተርሊንክ የሚገኝ ድጋፍ
ለሕጻናት ወይም አዋቂዎች በየእለቱ ክብካቤን የሚያደረጉ ተከባካቢዎች በየአሥራ አራት ቀኑ $123.50 ድጎማ ሊያገኙ ይችላሉ። ሌሎች ክፍያዎችና እገዛዎችን ለማግኘት የሴንተርሊንክን ግምገማ ማሟላት አለባቸው።

፭. የቋንቋና ትርጉም ግልጋሎቶች እገዛ
እገዛዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ከ Carers Australia ማግኘት ይቻላል። አስተርጓሚ የሚያሻም ከሆነ፤ የትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎትን በ 13 14 50 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል። ዝንቅ ባህልና ቋንቋ ያላቸውን በመርዳት ክህሎት ካለው የህሙማን ተከባካቢ እርዳታ ሰጪ መኮንንም እንዲሁ ድጋፍን ማግኘት ይቻላላ።

ተጨማሪ መረጃ የሚሹ ከሆነ Carers Australia ደረ-ገጽን ይጎብኙ አለያም በ 1800 242 636 ደውለው ይጠይቁ።
Share

