ሐኪም ዘንድ ቀርበው የጤና ምርመራዎችን ስለምን ሊያደርጉ እንደሚገባ ፱ ምክንያቶችን እነሆ።
፩. ስለ ጤንነትዎ ጠቅላላ ምርመራ ለማድረግ
ለጤና ምርመራ ሲሄዱ የሕክምና ታሪክዎን፣ የቤተሰብዎን የሕመም ታሪክና የአኗኗር ዘይቤን አስመልክቶ ሐኪምዎችዎ ሊጠይቅዎት ይችላሉ። መደበኛ የሆነ የደም፣ የሽንት፣ የዓይንና የልብ ምርመራ እንዲያደርጉ ሊያዙ ይችላሉ።
A stethoscope in the shape of a normal EKG graph

፪. የስኳር ሕመም ምርመራ ለማድረግ
280 አውስትራሊያውያን በየቀኑ ለስኳር ሕመም ይጋለጣሉ። አንድ ሰው በየአምስት ደቂቃዎች ማለት ነው። የስኳር ሕመም ምርመራ ደምዎ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ይለካል። የስኳር መጠን ምርመራው የሚካሄደውም ደምዎ ውስጥ ያለውን የጉሉኮስ ልክ ለመለካት ነው።
African woman using diabetes test kit

፫. የኮሌስትሮል ምርመራ ለማድረግ
፬. የደም ግፊት ምርመራ ማድረግ
ስር የሰደደ የደም ግፊት ለልብ ሕመም ምክንያቶች አንዱ ነው። በየስድስት ወሩ የደም ግፊት ምርመራ እንዲያደርጉ ምክረ ሃሳቦች ይሰጣሉ። ከ120/80mmHg በታች የሚነበብ የደም ግፊት ማለፊያ ተደርጎ ይወሰዳል።

፭. ክብደትዎን ይገምግሙ
ሁለት-ሶስተኛ አውስትራሊያውያን አንድም የሰውነታቸው ክብደት ከፍ ያለ ነው፤ አሊያም ውፍረታቸው አለቅጥ የበዛ ነው። ሐኪምዎችዎ ክብደትዎን ከቁመትዎ ጋር ለማነጻጸር የእርስዎን Body Mass Index ይገመግማሉ። ቁመትዎንና ክብደትዎን ማነጻጸሩ፤ ከተገቢው በታች ዝቅ ያለ ክብደት፣ ተገቢ ክብደት፣ ከተገቢው በላይ ከፍ ያለ ክብደት ወይም ክብደትዎ አልቅጥ ከፍ ያለ መሆኑን ግንዛቤ ያስጨብጥዎታል።

፮. የልብዎን አመታት መመርመር
Electrocardiogram (ECG) ልብ በሚመታበት ወቅት በልብ የሚመነጭን ኤሌክትሪካዊ እንቅስቃሴ የሚለካ ቀላል የሆነ የሕክምና ምርመራ ነው። ሐኪምዎ ልብዎን ለመመርመር የኤለክትሮካርዲዮግራም ምርመራ እንዲያደርጉ ሊያዝ ይችላል።
Close-up of an ECG report

፯. ክትባቶችና ተጨማሪ ክትባቶችን ለማግኘት
በአሁኑ ወቅት ክትባቶች በመላው ዓለም በዓመት ሶስት ሚሊየን ያህል ሕይወቶችን ያድናሉ ተብሎ ይገመታል። ክትባት ቀላል፣ ጥንቃቄን ያካተተ፣ ሕጻናትና አዋቂዎች በአጥቂ በሽታ ለጉዳት ከመዳረጋቸው በፊት የመከላከያ ፍቱን መንገድ ነው። 

፰. የቆዳ ምርመራ
The Cancer Council ከሶስት አውስትራሊያውያን ሁለቱ ዕድሜያቸው ፸ አመት ሲደርስ በቆዳ ካንሰር ሊጠቁ እንደሚችሉ ይገልጣል፤ በየዓመቱም አውስትራሊያ ውስጥ ከ 750,000 በላይ ሰዎች አንዴ ወይም ከዚያ በላይ ስር ያልሰደደ የቆዳ ካንሰር ሕክምና ያገኛሉ። ሐኪሞች ለየት ያለ የቆዳ ካንሰር ሊያስከትሉ ይችላሉ ብለው ካሰቡ የቆዳ ምርመራ እንዲደረግልዎት ያደርጋሉ።
Dermatologist examining patient for signs of skin cancer

፱. የአዕምሮ ጤናዎን ይከታተሉ
Beyond Blue ሶስት ሚሊየን አውስትራሊያውያን በመንፈስ ጭንቀት ውስጥ እንደሚኖሩ ይገልጣል። ሙያዊ የሕክምና እርዳታን ለማግኘት ከጠቅላላ የሕክምና ባለሙያ መጀመሩ ማለፊያ የመነሻ ነጥብ ይሆናል።

Share


