የአውስትራልይያ ቀን ትርጓሜ መነሻ ከአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ጅምር ላይ ነው። በአሁኑ ወቅት አያሌ ሰዎች የብሔራዊ ቀኑ ክብረ በዓል የነባር ዜጎችን ታሪክ ለመዘከርና ክብረ ሞገስ ለማላበስ ታላቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያምናሉ።
የአውስትራሊያ ቀን

'Founding Of Australia' -painting by Algernon Talmadge. Captain Arthur Phillip raises flag to declare British possession at Sydney Cove, Australia, 26 Jan 1788
የአውስትራሊያ ቀን የሚከበረው ጃኑዋሪ 26 1788፣ ካፒቴን አርተር ፊሊፕ የታላቋን እንግሊዝ ሰንደቅ ዓላማ ያውለበለበበትና የጃክሰን ወደብ (አሁን ሲድኒ ኮቭ ተብሎ የሚታወቀው) ላይ የእንግሊዝ ሥርወ መንግሥት የቅኝ ግዛትን ያወጀበትን ቀን ለመዘከር ነው።
ብሔራዊ የሕዝብ በዓል

IS tirade urges new attacks in Australia
የአውስትራሊያ ቀን እስከ 1994 ድረስ በመላው አገሪቱ በብሔራዊ የሕዝብ በዓልነት አይከበርም ነበር፡፡ ለብዙዎች ዕለቱ የማኅበረሰብ ትዕይንቶች መከወኛ፣ ወይም ከቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመዶች ጋር ሆኖ መብልና መጠጥ መቃመሻና የጓሮ ክሪኬት መጫወቻ ቀን ነው።
የዜግነት ቅበላ ሥነ ሥርዓት

በዕለተ ጃኑዋሪ 26 በመላ አገሪቱ የዜግነት ቅበላ ሥነ ሥርዓቶች ይካሄዳሉ።
ለበርካታ ሰዎች፣ የመጨረሻው የአውስትራሊያ ዜጋ የመሆኑ ደረጃ ቃልኪዳን መግባት ነው።
የወረራ ቀን

People marched throughout the nation on Australia Day 2016, and called for it to be renamed 'Invasion Day'
ለተወሰኑ አውስትራሊያውያን፣ በተለይም ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች፤ ጃኑዋሪ 26 የክብረ በዓል ቀን ተደርጎ አይወሰድም። ከቶውንም ዕለቱ የሚታየው የእንግሊዝ ሠፋሪዎች መሬቶቻቸውን በወረራ የነጠቁበት ሆኖ ነው።
የኃዘን ቀን

A picture of protesters on the Day of Mourning on January 26 in 1938.
በ1938፣ በ150ኛው የመታሰቢያ ክብረ በዓል ቀን፤ ዊሊያም ኩፐር፤ የነባር ዜጎች ተራማጅ ማኅበር አባልና ሌሎች ቀስቃሾች ተገናኝተው 'የኃዘንና የተቃውሞ ቀን' በሚል ዕለቱን አስበው ዋሉ።
ዕለቱ የአውስትራሊያውያን አቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ላይ በመንግሥት የውህደት ፖሊሲዎችና አያሌ ሰዎች ከመሬቶቻቸው በመነቀላቸውና ከባህላቸው በመነጠላቸው ሳቢያ የደረሰባቸውን የስነ ልቡና ድቅቀትን አካትቶ ለታሪካቸውም ዕውቅናን ይቸራል።
የነባር ዜጎች ሉዓላዊነት

Indigenous Sovereignty
የወረራ ቀን ለነባር ዜጎች የሉዓላዊነትን ጥያቄ መግፊያ መልካም አጋጣሚ ተደርጎም ይታያል። በየዓመቱ የአውስትራሊያ ቀን ክብረ በዓልን በመቃወም በመላ አገሪቱ በሚገኙ ከተሞች የአውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ሉዓላዊነትና ማህበራዊ ፍትሕን እንዲቀዳጁ ሰልፍ በማካሄድ ጥሪ ይቀርባል።
ዕለተ ቀኑን መለወጥ ለምን ያስፈልጋል?

ክብረ በዓሉ ሌሎች አገራት እንደሚያከብሩት የነፃነት ቀን ወይም ልዩ ብሔራዊ ክብረ በዓል ቀን ተደርጎ ሳይሆን የሚታየው ከቶውን በቅኝ ግዛት ቀንነት ነው።
"ሁላችንንም ያካተተ ሰሜት የሚያሳድርብንን፣ ሁላችንም በእኩልነት የምንሳተፍበትና በጋራ አውስትራሊያዊ ማንነት በኩራት ማክበር የምንችልበትን ቀን እስቲ እንፈልግ።" - Lowitja O’Donoghue, የ1984 የዓመቱ የአውስትራሊያ ሰው።
ዕለተ መድኅን

ለበርካታ አቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች፣ የአውስትራሊያ ቀን የሰዎቻቸውና ባህላቸው በአይበገሬነት ለትድግና መብቃትን ዕውቅና የማግኛ መልካም አጋጣሚምም ተደርጎ ይታያል።
“ዘጠና ፐርሰንት ሰዎች የአውስትራሊያ ቀን የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎችን ባሕሎች ማካተት አለበት ይላሉ። አንድ ቀን ሁሉንም አውስትራሊያውያን በምልዓት አካታች የሆነ ቀን እንመርጣለን ብዬ በፅኑዕ አምናለሁ።” - Mick Dodson የሕግ ፕሮፌሰርና የ2009 የዓመቱ አውስትራሊያ ሰው።