Settlement Guide: How do I access public dental care in Australia?

ከልጅነት ጀምሮ በየጊዜው መደበኛ የጥርስ ምርመራ ማድርግ በጉልምስና ዕድሜ ላይ ለጥርስ ጤንነት ይረዳል። ይሁንና፤ ሜዲኬር የሚሸፍነው ጠቅላላ ጤናን ለመታደግ አስፈላጊ የሆኑ ውስን የጥርስ ሕክምና አገልግሎቶችን ብቻ ነው።

Settlement Guide: How do I access public dental care in Australia?

Source: AAP

እናም፤ መመዘኛውን የሚያሟላው ማን ነው - ሌሎች አማራጮችስ አሉ?

የሕዝብ የጥርስ ግልጋሎቶችን የት ፈልጎ ማግኘት ይቻላል?

at_the_dentist_-_getty_images_1.jpg?itok=s0R3J8HP&mtime=1489444926


 

Male Patient Receiving Treatment In Clinic

የሕዝብ የጥርስ ግልጋሎቶች በአብዛኛው ግልጋሎታቸውን የሚሰጡት በተንቀሳቃሽ የጥርስ ክሊኒኮች፣ በትምህርት ቤት የጥርስ ክሊኒኮችና በማኅበረሰብ የጥርስ ክሊኒኮች አማካይነት ነው። በክልልዎ ወይም ክፍለ ግዛትዎ ስላሉ የሕዝብ የጥርስ ግልጋሎቶች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ካሹ State Health Department's website ይጎብኙ።

ብቁ የሚሆነው ማን ነው?



እያንዳንዱ ክልል በመጠኑ ለየት ያለ መመዘኛ አለው፤ ይሁንና ከ Centrelink, የተሰጠዎት የጤና ክብካቤ ካርድ፣ የጡረተኛ ካርድ፣ እንዲሁም በ Department of Veterans' Affairs የታደለ የጋራ ብልፅግናው የጡረተኞች የጤና ካርድና የተጠዋሪ ቅናሽ ካርድ ካለዎት፤ እርስዎ በሕዝብ ለሚደጎም የጥርስ ክብካቤ ተጠቃሚ ለመሆን መመዘኛውን ያሟላሉ። ለምሳሌ ያህል፤ ቪክቶሪያ ውስጥ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ነጻ ክብካቤ ያገኛሉ።

ሕጻናትና ወጣቶችን በተመለከተስ?

teeth_kids_flickr.jpg?itok=2j2PPRQE&mtime=1489445127


ሜዲኬር የሚሸፍናቸው አውስትራሊያውያን ሕጻናት የአውስትራሊያ Government's Child Dental Benefits Schedule ተጠቃሚ ይሆናሉ። ምንም እንኳ ከክልል ክልል የተለያየ ቢሆንም በጥቅሉ ሕጻናት ዕድሜያቸው አሥራ ስምንት እስከሚደርስ ድረስ በተወሰነ የቤተሰብ ታክስ ድጎማ ስር እስካሉ ድረስ መመዘኛውን የሚያሟሉ ይሆናሉ። እንደ ኩዊንስላንድ ያሉ የተወሰኑ ክልሎች ሕጻናትና ወጣቶች ምርመራ ከማድረጋቸው በፊት የሕክምና ታሪክና የስምምነት ፎርም አስቀድመው እንዲሞሉ ግድ ይሰኛሉ። የስምምነት ፎርሙ እስከ 20 በሚደርሱ የማህበረሰብ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይገኛል።

የግል ሕክምናን መጠቀም?

co-located-service-centre-outdoor-signage_dept_human_services.jpg?itok=jyhQlgZG&mtime=1489445724


የጥርስ ሕክምና ግልጋሎቶችን ክፍያ በተመለከተ፤ እንደ ጥርስ ሐኪሙና እንደሚኖሩበት አካባቢ ይወሰናል። መልካም የጤና ኢንሹራንስ ወጪን ይቀንሳል፤ ይሁንና ሁሉንም ወጪ የሚሸፍን አይደለም። የጤና ኢንሹራንስ ደንበኞች ከጥርስ ሕክምና ወጪያቸው ተመላሽ የሚሆንላቸው በአማካይ ግማሽ ያህሉ ነው።

ኢንሹራንስ የሌለዎት ከሆነ ምን ሊያደርጉ ይገባል?

dentist_school_aap.jpg?itok=Qy-7NgCF&mtime=1489445839


በጀትዎ አነስተኛ ከሆነ የሕክምና ምርመራውን ከመጀመርዎ በፊት ከጥርስ ሐኪምዎ ጋር ወጪዎችን አስመልክቶ መነጋገሩ በጀትዎን ለመበጀት ይረዳዎታል።

ወጪዎን እንደምን መቀነስ ይቻላሉ?

ከ dentistry school ጋር ቀጠሮ ሊይዙ ይገባል። በጥቅሉ ከሌሎች የግል ሕክምና ሰጪዎች ይልቅ ክፍያቸው አንስተኛ ስለሆነ ገንዘብዎን ሊቆጥቡ ይችላል።

ተጨማሪ መረጃ?

በክልልዎ ወይም ክፍለ ግዛትዎ ስላሉት የሕዝብ ጥርስ ግልጋሎቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፤ የክልልዎን የጤና ዲፓርትመንት ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

 


Share
2 min read

Published

By Ildiko Dauda
Presented by Kassahun Seboqa

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service