Settlement Guide: Living with a Disability in Australia - 7 tips for accessing services

የብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድ፤ የግብረ-አካል ጉዳተኞች ለሕይወታቸው ምልዓት ለሚሹት ድጋፍ ምርጫና ይሁንታ ሰጪ ዕድል ይቸራቸዋል።

NIDS

A family who are NDIS ready for the National Disability Insurance Scheme (National Disability Insurance Agency) Source: NIDS

ስለ ብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድ ሊያውቋቸው የሚገባዎትን ፯ መዘርዝረ ዕውንታዎች እነሆ።

የብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድ ደረጃ በደረጃ በመላው አውስትራሊያ ከጁላይ 2016 ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

 

የተቋቋመው በሌበር መንግሥት በ2012 ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ተግባሩን የሚከውነው በ2019 ነው። ለምሳሌ ያህል፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ልዩ የግብረ-አካል ጉዳተኞች ድጋፎችን እያገኙ ያሉ በርካታ ሰዎች ቀላል ግልጋሎት ማግኛ ሂደትን በመጠቀም በእያንዳንዱ ሁለት የትግበራ ዓመታት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ የብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ።

የብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድ የእድሜ ልክ አሰራርን ይጠይቃል፤ የግብረ-አካል ጉዳተኞች በጉልምስና የሕይወት ዘመናቸው ማለፊያ ውጤትን እንዲቀዳጁ ቀደም ካለው የሕይወት ዘመናቸው ጀምሮ እገዛ ማድረጉ ማለፊያ ተግባር ነው።

 

የግለሰብን መሠረታዊ ፍላጎቶች መሠረት ያደረገ የብሔራዊ ግብረ-አካል ኢንሹራንስ ዕቅድ ትልም ግቦችዎን ለስኬት እንዲያበቁ ያግዝዎታል። በቅድሚያ ምን እንደሚሹ ያስቡ፤ ቀጥለው ከብሔራዊ ግብረ-አካል ኢንሹራንስ ዕቅድ ትልም ነዳፊዎን በማግኘት ፕላንዎን ያዳብሩ።

1d0f0eb6-8a2a-4b47-9b8c-fec5d1074505_1480465410.jpeg?itok=Pu4UXL6K&mtime=1480465429

Jack - an early enlister in the National Disability Insurance Scheme

የዕቅዱ ተጠቃሚ የሚሆኑት የማይሽር የግብረ-አካል ጉዳተኛ በመሆንዎ ሳቢያ የዕለት-ተዕለት ተግባራትን ለመከወን የማይችሉ የሆኑ እንደሁ ነው።
የአውስትራሊያ ዜጋ ሊሆኑ ይገባዎታል ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊኖርዎት ግድ ይላል አሊያም ልዩ ጥበቃ የሚያስገኝልዎት የቪዛ መደብ ያሻዎታል።
215ead91-9c1b-431c-b7dd-499680e15ff8_1480465449.jpeg?itok=BBeZW06B&mtime=1480465461
ዕድሚዎ ከ65 ዓመት በታች የሆነና ዕቅዱ ግልጋሎቱን በሚሰጥበት የአውስትራሊያ ክፍለ ግዛት ነዋሪ መሆን አለብዎት።
ndis_2_resized.jpg?itok=xcCW5nj5&mtime=1480465497
የብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ዕቅድን የሚተገብረው የጋራ ብልፅግናው ብሔራዊ የግብረ-አካል ጉዳተኞች ኢንሹራንስ ኤጀንሲ ነው።

ለምሳሌ፤ በአሁኑ ወቅት ቪክቶሪያ ውስጥ የድጋፍ ግልጋሎቶችን የሚያገኙ ከሆነ ወደ ብሔራዊ ግብረ-አካል ኢንሹራንስ ዕቅድ ለመሸጋገር የሚያስችልዎትን ሂደት ለመከወን በጋራ ብልጽግናው የግብረ-አካል ጉዳተኞች ኤጀንሲ በኩል ለውይይት ጥሪ ይቀርብልዎታል።

25aae479-e226-464c-b32c-726aff0f3618_1480465525.jpeg?itok=w2gyH6Ob&mtime=1480465535
በአካባቢዎ ከሚገኘው የብሔራዊ ግብረ-አካል ጉዳተኞች ኤጀንሲ ጋር ግንኙነት ሊያደርጉ ይገባዎታል።

The Action on Disability within Ethnic Communities ዕቅዱን ለመተግበር ከተመዘገቡት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው። ከዚያም ባሻገር ሰዎች ቀደም ያለ ዕቅድ የተነደፈለት ሂደት ድጋፍን በቀጥታ ማግኘት እንዲቻላቸው advocacy support program እገዛን ያደርጋል።

f3912d55-f9b1-4090-96e2-ae650483031c_1480465563.jpeg?itok=XOIGFY8o&mtime=1480465572

Aran, a participant in the NDIS

ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ካሹ NDIS in Victoria እና NDIS in NSW የመረጃ ቋጠሮን ይጎብኙ፡፡ በአካባቢዎ ስላለው የክንውን ሂደት ለመረዳት ከፈልጉም NDIS ድረ-ገጽን ይጎብኙ ወይም 1800 800 110 ይደውሉ። እንዲሁም መረጃዎች በተለያዩ ቋንቋዎች ተዘጋጅተዋል different languages ።

መስማትና መናገር የተሳናቸው TTY: 1800 555 677

የሚናገሩና የሚሰሙ፤ 1800 555 727

ለጽሁፍና የቃል ትርጉም አገልግሎቶች TIS: 131 450 ይደውሉ።

በ Facebook/NDISAus ወይም በ Twitter @NDIS መረጃን ማግኘት ይችላሉ።

 


Share

2 min read

Published

By Ildiko Dauda

Presented by Kassahun Seboqa



Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service