የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት ላይ ድምፅዎን የሚሹ በርካታ ዕጩዎችን ይዞ ይገኛል።
ከአነስተኛ ፓርቲዎች ውስጥ ከፍ ያለ ደጋፊዎች ስቦ ያለው ግሪንስ ፓርቲ ነው።
ዘጠኝ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላትና አንድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አሉት።
የግሪንስ ፓርቲ ማኅበራዊ ተራማጅ አቋም ያለው ሲሆን፤ በዘንድሮው ምርጫ የአዕምሮ ጤናና የጥርስ ሕክምና ሜዲኬይር ውስጥ እንዲታከል እየገፋ ነው።
እንዲሁም፤ የደንጊያ ከሰልና ጋዝ በታዳሽ ኃይል እንዲተካና ከአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ጋር የቃል ኪዳን ስምምነት እንዲደረግ ይሻል።

Greens leader Adam Bandt (C) claps during the Greens national campaign launch at Black Hops Brewery on May 16, 2022 in Brisbane, Australia. Source: Getty
ግሪንስ ፓርቲ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ከደጋፊዎቹ የሚያገኙ ሁለተኛ አማራጭ ድምፆች በሙሉ ለሌበር ፓርቲ እንዲሸጋገር ያደርጋል።
***
የተባበሩት አውስትራሊያ ፓርቲ የተመሠረተውና በገንዘብም የሚደገፈው በቢሊየነር ክላይቭ ፓልመር ነው።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወክሎ ያለው በቀድሞው የሊብራል ምክር ቤት አባል ክሬይግ ኬሊ ነው።
በዘንድሮው ምርጫ ሰፊ የምርጫ ማስታወቂያዎችን እያሰራጨ ነው።
በዘንድሮው ምርጫ 70 ሚሊየን ዶላርስ ያህል ወጪ ማድረጉን ክላይቭ ፓልመር አስታውቀዋል።
የተባበሩት አውስትራሊያ ፓርቲ ገደቦችን የመክላት የነፃነት አቋሞችን የሚያራምድ ሲሆን፤ በአንኳር ፖሊሲነትም:-

Clive Palmer, Chairman of The United Australia Party. Source: Getty
- አስገዳጅ የኮቪድ-19 ክትባት መኖር የለበትም
- ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሳንሱር መደረግ የለበትም
- የቤት ብድር ወለድ መጠን ከሶስት ፐርሰንት እንዳያልፍ ይሻል።
የተባበሩት አውስትራሊያ ከደጋፊዎቹ የሚያገኙ ሁለተኛ አማራጭ ድምፆች ለሊብራል ፓርቲ እንዲሰጡ ይሻል፤ ሆኖም በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር ፒተር ዳተን ተይዞ ላለው የኩዊንስላንድ ዲክሰን ምክር ቤት ወንበር ደጋፊዎቹ አማራጭ ድምፃቸውን እንዲሰጡ አያበረታታም።
***
ዋን ኔሽን ፓርቲ የተመሠረተው በ1990ዎቹ መገባደጃ በፖሊን ሃንሰን ነው።
ሁለት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወንበሮችን ይዞ ይገኛል።
ዋን ኔሽን ከሚያራምዳቸው አቋሞች አንዱ ፀረ-ክትባት አቋም ነው።
ወደ አውስትራሊያ የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንዲቀንስ ይፈልጋል።
እንዲሁም፤ አውስትራሊያ ከተባበሩት መንግሥታት የ2016 የፓሪስ አየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንድትወጣ ይሻል።

A cut-out of Pauline Hanson is displayed on February 19, 2022 in Geraldton, Australia. Western Australia. Source: Getty
ዋን ኔሽን ሁለቱን ዋነኛ ፓርቲዎች ይቃወማል።
ደጋፊዎቹ አማራጭ ድምፆቻቸውን የግሪንስ ፓርቲን መጨረሻ በማድረግ ለአነስተኛ ፓርቲዎች እንዲሰጡ ያበረታታል።
ሙሉ የፓርቲዎቹ ፖሊሲዎች በየድረ-ገጾቻቸው ይገኛሉ።