ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በውስጥ ጉዳያችን ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን አንቀበልም አሉ ፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ሁሉ ፈርጀ ብዙ የሆኑትን አለም አቀፍ ህጎችን እና ደንቦች ስታከብር መቆየቷን አስታውሰው በተመሳሳዩም ፤ ኢትዮጵያ ህግን እና ስርአትን በማስከበር ሂደት ውስጥ ባለችበት በአሁኑ ውቅት ፤ የአለም አቀፉ ማህበረስቡ ለመርዳት ያሳየውን ፍላጎት አድንቀዋል፡፡ ይሁንና አካሄዱ በተመለከተ በአለማቀፍ ህግ መሰርት እንዲከናውውን አሳስበዋል፡፡
በዚህም መሰርት የኢትዮጵያ መንግስት የእርዳታ ጥሪን እስኪያቀርብ ድረስ የአለም አቀፉ ማህበረስብ ከማንኛውም አይነት ጣልቃ ገብነት ታቅቦ መጠበቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአሁን ሰአት ያለባትን ችግር የአለም አቀፍ መርሆዎችን በተከተለ መልኩ ለመፍታት አቅሙ እንዳላትም አሳስበዋል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም ምንም እንኳ የአጋሮቻችንን ስጋት እና ምክር ከግምት ውስጥ ብናስገባም ፤ በውስጥ ጉዳያችን ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ግን ሙሉ በሙሉ አንቀበለውም ብለዋል ፡፡በስተመጨረሻም “ ከበሬታን በተሞላው መልኩ የምናገረው ነገር ቢኖር ፤ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ካልታጋበዙት ከማንኛውም አይነት ህገ ወጥ ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠቡ ፤ እንዲሁም መሰረታዊ የሆነውን ህግ እንዲያከብሩ ነው ፡፡” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ ር አብይ አህመድ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት መልእክት ፡፡