ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጥር 12 ቀን 2015 የሶስት ዕጩ ሚኒስትሮችን ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅድቅ እንዲቸረው ጠየቁ።
በዚህም መሠረት፤
1. ዶ/ር ዓለሙ ስሜ - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
2. ኢንጂነር ኃብታሙ ተገኝ - የማዕድን ሚኒስትር
3. ዶ/ር ግርማ አመንቴ - የግብርና ሚኒስትር ሆነው በዕጩነት ቀርበዋል።
ከጥር 10 ቀን 2015 አንስቶም የብሔራዊ ባንክ ገዢና በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ አማካሪ ሹመኞች ሹመቶቻቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፅድቅ ውሳኔ አግኝቷል።
1. አቶ ማሞ ምህረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ
2. ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር
4. አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ - የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር
5. አቶ መለሰ ዓለሙ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው ተሾመዋል።