የአውስትራሊያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ሶኮሩስ ዴንማርክን 1 ለ 0 በመርታት ለቀጣዩ የፊፋ ዓለም ዋንጫ 2022 አለፈች።
አውስትራሊያ በቀጣይነት ከቡድን C አሸናፊዎች አርጀንቲና ወይም ሜክሲኮ ጋር ለጥሎ ማለፍ ውድድር ተጋጣሚነት ትቀርባለች።
አውስትራሊያ ቀደም ሲል በዓለም ዋንጫ ውድድር 16 ቡድናት ለሚፋለሙበት ጥሎ ማለፍ ያለፈችው በ2006 ከክሮኤሽያ ጋር በአቻ ውጤት ተለያይታ ነው።
የአውስትራሊያ ቡድን ደጋፊዎች ከንጋቱ 2am AEDT በሜልበርን ፌዴሬሽን አደባባይ ከትልቅ የፊልም ስክሪን ፊት ለፊት ታድመው ድጋፋቸው ገልጠዋል።
ሌሎችም በየቡና ቤቱ ተሰባስበው ድጋፋቸውን በሆታ ቸረዋል።
ኳታር ያሉ አውስትራሊያንም ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን ስትረታ እንዳደረገችው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚንም ለአውስትራሊያውያን የአንድ ቀን አገር አቀፍ የሥራ ዕረፍት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤
ቱኒዚያ ፈረንሳይን 1 ለ 0
አርጀንቲና ፖላንድን 2 ለ 0
ሜክሲኮ ሳዑዲ አረቢያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።