ዛሬ ማክሰኞ ኖቬምበር 1 / ጥቅምት 22 በተካሔደው 162ኛው ዓመታዊ የፈረስ ውድድር የአምስት ዓመቱ ፈረስ ጎልድ ትሪፕ አሸናፊ ሆኗል።
የ3200 ሜትሮች ውድድሩን ጋልቦ በአንደኛነት የጨረሰው ፈረስ ጋላቢ ማርክ ዛህራ የውድድር ማብቂያ መስመሩን በፈረሱ ጋልቦ ሲያቋርጥ "የማይታመን" "እንዴት ያለ ቀን። አጠገቤ የተጠጋ እንኳ የለም" ብሏል።
በሌላም በኩል የእንሰሳት መብቶች ተሟጋቾች ባለፈው የፈረሰ ውድድር ዓመት 139 ፈረሶች ለሞት መዳረጋቸውን ዋቤ ነቅሰው የተቃውሞ ድምፆቻቸውን አሰምተዋል።
80 ሺህ ያህል የስፖርቱ አፍቃሪዎች በታደሙበት የሜልበርን ፍሌሚንግተን ዓመታዊ የፈርስ ግልቢያ እሽቅድምድም ዓመቱን ቆጥሮ የፋሽን ትዕይንት ቀርቧል።
በ60ኛው የማየር ፋሽን ትዕይንት ታዋቂ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሞዴሎች በትዕይንቱ ተሳትፈዋል።

Fashions on The Field Best Suited finals during 2022 Melbourne Cup Day at Flemington Racecourse on November 01, 2022 in Melbourne, Australia. Credit: Naomi Rahim/Getty Images for VRC

Anna Heinrich and Tim Robards (L), Delta Goodrem (C), and Adut Akech (R). Credit: Sam Tabone/Getty Images

Racegoers brave the rain during 2022 Melbourne Cup Day at Flemington Racecourse on November 1, 2022 in Melbourne, Australia. Credit: Martin Keep/Getty Images for VRC