በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሓት መካከል ተከስቶ ላለው ግጭት ዕልባት ለማበጀት ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እየተካሔደ ያለው የሰላም ንግግር የደረሰበትን ደረጃና ቀጣይ ሂደት አስመልክቶ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰTeውም በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ከፍተኛ የምሥራቅ አፍሪካ ልዑክ ተወካይ ኦሉሴንገን ኦባሳንጆ መሆኑ ተነግሯል።
የሰላም ንግግሩ የተካሔደው በኦባሳንጆ መሪነት፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚደንት ኡኹሩ ኬንያታና የደቡብ አፍሪካ የቀሞዋ ምክትል ፕሬዚደንት ፉምዚሌ ምላምቦ ንጉካ ረዳትነት ሲሆን፤ በተሳታፊነትና ታዛቢነትም የኢጋድ፣ ተመድና ዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ተገኝተዋል።