አውስትራሊያና አርጀንቲና በኳታር አሕመድ ቢን አሊ ስታዲየም ባካሔዱት የፊፋ ዓለም ዋንጫ 2 ለ 1 ተለያይተዋል።
አርጀንቲናን ከኔዘርላንድስ ጋር ለቀጣዩ ሩብ ፍፃሜ ፍልሚያ እንዲያልፍ ያደረጉትን ግቦች ያስቆጠሩት ሊዮኔል ሜሲ 35' እና ሁሊያን አልቫሬዝ 57' ሲሆኑ፤ ኢንዞ ፊማንዴዝ ለአውስትራሊያ በ77ኛው ደቂቃ አንድ ግብ አስቆጥሯል።

ሽንፈቱ የአያሌ አውስትራሊያውያንን ልብ ቢሰብርም ብሔራዊ ቡድናቸው ሶኮሩ ለጥሎ ማለፍ በቅቶ ብርቱ ፍልሚያ በማድረጉ ከፍ ያለ ኩራት ተሰምቷቸዋል፤ የላቀ አድናቆታቸውንም ቸረዋል።
የአውስትራሊያ እግር ኳስ ቡድን ሶኮሩም ምስጋናውን ለአውስትራሊያ ሕዝብ አቅርቧል "እናመሰግናለን አውስትራሊያ" ሲል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚም አድናቆታቸውን ገልጠዋል።
የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ሠንጠረዥ
ፈረንሳይ እና ፖላንድ (ሰኞ ዲሴምበር 5 / ሕዳር 26) 2:00 am [AEDT]
እንግሊዝ እና ሴኔጋል (ሰኞ ዲሴምበር 5 / ሕዳር 26) 6:00 am [AEDT]
ጃፓን እና ክሮኤሽያ (ማክሰኞ ዲሴምበር 6 / ሕዳር 27) 2:00 am [AEDT]
ሞሮኮ እና ስፔይን (ረቡዕ ዲሴምበር 7 / ሕዳር 28) 2:00 am [AEDT]
የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ሠንጠረዥ
ኔዘርላንድስ እና አርጀንቲና (ቅዳሜ ዲሴምበር 10 / ታሕሳስ 1) 6:00 am [AEDT]

