በተጫዋችነቱ ዘመን "የእግር ኳስ ንጉሥ" ተብሎ ይወደስ የነበረው የ82 ዓመቱ ፔሌ በሳኦ ፓውሎ አልበርት አንሽታይን ሆስፒታል እያገገመ እንደሚገኝ የሆስፒታል ምንጮች ገልጠዋል።
የካንሰር ሕመም ተጠቂው ፔሌ ባለፉት 24 ሰዓታት የመተንፈሻ አካል ሕክምና እንደተደረገለትና እያገገመ ያለ መሆኑንም የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ገልጠዋል።
ፔሌ መልካም ምኞታቸውን ለገለጡለት ሁሉ ከ10 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ባሉት የኢንስታግራም ገጹ ምስጋናውን አቅርቧል።
ኤድሰን ኤራንተስ ዶ ናሲመንቶ ወይም በፖርቹጋል አጠራር "ፔሌ" በኢትዮጵያውያን ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ዝናው የገነና በፊፋም "የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ የእግር ኳስ ተጫዋች" ተብሎ የተሰየመ ነው።
በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኑ ከተጫወታቸው 1,363 ግጥሚያዎች 1,279 ግቦችን በማስቆጠር የዓለም ሬኮርድ ባለቤት ሆኗል።
ፔሌ ለብራዚል የ1958፣ 1962 እና 1970 የፊፋ ዓለም ዋንጫን በአሸናፊነት በማስገኘት ብቸኛው ተጫዋች ነው።

World Cup Final 1970, Mexico City, Mexico, 21st June, 1970, Brazil 4 v Italy 1, Brazil's Pele takes a free kick as Italian players form a wall during the World Cup Final. Credit: Rolls Press/Popperfoto via Getty Images/Getty Images