የትምህርት ሚኒስቴርና ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ለማካተት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕወሓት አመራሮች ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ

Dr Daniel Bekele and Prof Berhanu Nega.jpg

Dr Daniel Bekele, Chief Commissioner of the Ethiopia Human Rights Commission (L), Prof Berhanu Nega, Minister of Education (R). Credit: Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency via Getty Images / EDUARDO SOTERAS/AFP via Getty Images

የሰብአዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ሥርዓቶች ውስጥ በአግባቡ ለማካተትና ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መካከል ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ተፈርሟል።

ስምምነቱ የሰብዓዊ መብቶች ዕሴቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ከማስረፅ አኳያ ተደራሽነትን በመጨመር በኢትዮጵያ ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰብዓዊ መብቶች ባሕልን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጣምራ ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ስምምነቱ፤ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ሥርዓቶች ውስጥ በአግባቡ እንዲካተት፣ እንዲጠናከር እና እንዲስፋፋ በጋራ መሥራትን፤ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት በተጓዳኝ የትምህርት መንገዶች በተለይም በክለቦችና በሌሎች የማስተማሪያ ማእቀፎች ለተማሪዎች የሚደርስበትን ሁኔታ ማመቻቸት እና ከሌሎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር መተባበር የሚሉ ዝርዝር ዓላማዎችን ማካተቱ ተጠቅሷል።

በመግባቢያ ስምምነቱ መሠረት የትምህርት ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን አመቺ በሆኑ የትምህርት ዓይነቶች በተለይም በግብረ-ገብና በዜግነት ትምህርቶች በግልፅና ትርጉም ባለው ደረጃ መካተታቸውን ለማረጋግጥ እና በተጓዳኝ የትምህርት ዘርፎችም እንዲሰጥ ይሠራል።

ተፈራራሚዎቹ በተጨማሪም በመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ሥራ ላይ ያሉ ሥርዓተ-ትምህርቶች እና የስልጠና መጻሕፍት ይዘት በተሟላ መንገድ የሰብአዊ መብቶችን ፅንሰ-ሃሳብና መርሆች እውቀት የሚያስጨብጥ መሆኑን ለማረጋገጥ እና በየዓመቱ ኮሚሽኑ የሚያካሂደውን ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ምስለ ፍርድ ቤት (Moot Court) ውድድር በተመለከተ አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ እንደሚሠራ በስምምነቱ መካተቱን አመላክተዋል፡፡

በስምምነቱ መፈራረሚያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “የሰብአዊ መብቶች እሴቶችንና መርሆችን ተገንዝቦ በዕለት ተዕለት ግንኙነቱና በባህሪው የሚያንፀባርቅ ትውልድ መፍጠር፤ በመከባበር፣ በመቻቻልና በመግባባት በሰላም አብሮ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብን ለመገንባት የሚያስችል እርምጃ ነው” ብለዋል። አክለውም ዘላቂ የልማት ግብ 4.7ን (ትምህርት ለዘላቂ ልማትና ለዓለም አቀፋዊ ዜግነት/Education for sustainable development and global citizenship) ለማሳካት ከፍ ያለ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ሲሉ አብራርተዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ሲሆኑ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለን ጨምሮ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የሕወሓት አመራሮች

የፌዴራል መንግሥት እና የሕወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በሐላላ ኬላ ተገናኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ መቀመጡም ተነግሯል።
Leaders.jpg
Federal and TPLF leaders meeting in Halala, Ethiopia, on February 4, 2023. Credit: PR

የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ያደረጉት የገበታ ለአገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሐላላ ኬላ ነው።

Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service