በእግር ኳስ ጥበቡ ከሕይወት በላይ ግዘፍ ነስቶ የነበረው የብራዚላዊው ፒሌ የቀብር ሥነ ሥር ዓት ተፈፀመ።
ፒሌ ከዚህ ዓለም በ82 ዓመቱ በሞት የተለየው ለአንድ ዓመት ያህል ከካንሰር ጋር ሲፋለም ቆይቶ ነው።
አዲሱን የብራዚል ፕሬዚደንት ሉላን ጨምሮ 230,000 ያህል ለቀስተኞች በሳንቶስ እግር ኳስ ክለብ ቪላ ቤልሚሮ ስታዲየም ተገኝተው አስከሬኑን ተሰናብተዋል።
ፕሬዚደንት ሉላ ከእንግዲህ የቀድሞ የእግር ኳስ ፊልሞቹን በማየት ካልሆነ በስተቀር ዳግም ላያዩት በስታዲየም ተገኝተው ለመጨረሻ ጊዜ መሰናበታቸው ያሳደረባቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጠዋል።
አክለውም፤ ጭፍን ጥላቻ እስካሁን ገንኖ ባለባት አገር ደሃ፣ ጥቁር ሆኖ ለተወለደው ሰው "ዓለም ክብርን የማላበስ ዕዳ አለባት" ብለዋል።
ማሊ
የማሊ የደኅንነት ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ በመዲናይቱ ባማኮ አንድ የሲቪል መከላከል ተቋም ባለበት አቅራቢያ ባልታወቁ ሰዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶች አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገለጠ።
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጎ ያነሳው አካል የለም።
የማሊ ማዕከላዊና ሰሜናዊ ክፍለ አገራት በእስላማዊ አማፅያን ታውኮ ይገኛል።
ምንም እንኳ መግለጫው ዝርዝር ማብራሪያዎችን ባይሰጥም፤ በጥቃቱ ሕይወታቸውን ካጡት ግለሰቦች ውስጥ ሁለቱ የሲቪል መከላከል ኃይል አባላት ሲሆኑ፤ ሶስቱ ሰላማዊ ሰዎች እንደሆኑ አመልክቷል።