የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ሜይ 3 ባወጡት መግለጫ ኤጄንሲው "የምግብ እርዳታውን ለትግራይ ክልል ለመግታት አዋኪ ውሳኔ ወስኗል" ሲሉ አስታወቀዋል።
መግለጫው፤ ኤጄንሲው ምንም እንኳ የወሰደው እርምጃ አዋኪ ቢሆንም፤ በረሃብ ለተጎዱ የትግራይ ሕዝብ አስቦ ያቀረበው የምግብ እርዳታ ወደ ገበያ ወጥቶ ለሽያጭ መቅረቡ ችሮታውን ለመግታት ግድ እንዳሰኘው ገልጧል።
አክሎም፤ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጄንሲ ጉዳዩን እንደደረሰበት ለዋና ተቆጣጣሪ የመራ መሆኑንና ገዲብ አመራሮች በሥፍራው ተገኝንተው ያካሔዱትን ምርመራ ተከትሎ በደረሰበት የፕሮግራሞች ክለሳ መሠረት የምግብ እርዳታውን በጊዜያዊነት መግታት ተመራጭ ግብራዊ እርምጃው አድርጎ ለመሰድ እንደበቃ አመላክቷል።
ጉዳዩን አስመልክቶም፤ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለ ስልጣናት ማቅረቡንና ኃላፊነቱ የሚመለከታቸውን ለይተው ተጠያቂ እንደሚያደርጉ የተነገረው መሆኑም ተነግሯል።
ኤጄንሲው የገታውን የምግብ እርዳታ ዳግም የሚጀምረው ጠንካራ የቁጥጥር እርምጃዎች ግብር ላይ ሲውሉ ብቻ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥቶ አሳስቧል።
አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የትግራይ ክልል ጊዘያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት በበኩላቸው በከፍተኛ ደረጃ" ምርምራ ማስጀመራቸውን ገልጠው፤ ዓለም አቀፉ የረድኤት ድርጅቶች በዘርፈ ብዙ ልገሳቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።