የዓለም ዋነኛና ባለ ኢንዱስትሪ አገራት ቡድን 7 ገዲብ ዲፕሎማቶች ለሁለት ቀናት ውይይት በምዕራብ ጀርመን ሙኢንስተር ከተማ ታድመዋል።
የንግግራቸው ትኩረት በሩስያና ዩክሬይን ጦርነት ሳቢያ በተከሰቱት የምግብና የኃይል ምንጭ እጥረቶች፣ እንዲሁም ከአውሮፓ ርቆ ባሳደራቸው ተፅዕኖዎች ላይ ነው።
ታዳሚዎቹ የቡድን 7 አገራት እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓንና ዩናይትድ ስቴትስ ናቸው።
ኢምራን ከሃን
የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ከሃን ላይ የመግደል ሙከራ በማድረግ ተጠርጣሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ማንነቱ ይፋ ያልሆነው ተጠርጣሪ ግለሰብ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመግደል እንደሞከረና ያንንም ያደረገው ያለ ማንም እገዛ ብቻውን እንደሆነ ተናግሯል።
እግራቸው ላይ የመቁሰል አደጋ የደረስባቸው የ70 ዓመቱ ከሃን በአሁኑ ወቅት በሻዩካት ከሃኑም ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን፤ ቀዶ ሕክምና የተደረገላቸውና በደኅና ሁኔታም የሚገኙ መሆኑን ዶ/ር ፋይዛል ሱልጣን ገልጠዋል።
ከሃን በጥይት የግድያ ሙከራ የደረሰባቸው የተቃውሞ ሰልፍ ተገኝተው ባሉበት ወቅት ነው።